አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2017(ኢዜአ)፡-የዲጂታል አትዮጵያ ግንባታን ለማፋጠን አገር በቀል ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን የማልማት ስራን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተሳታፊዎች ገለጹ።
ኤክስፖው በርካታ ልምድ ያገኙበት መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ያዘጋጁት በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 በአዲስ አበባ ተከፍቷል፡፡
በብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ሱፐርቫይዘር የሆኑት በርናባስ መኮንን፤ ኢትዮጵያ በዲጂታል መታወቂያ እያከናወነችው ያለው ውጤታማ ተግባር በኤክስፖው መቅረቡን ተናግረዋል፡፡
ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታና ሁለንተናዊ ዕድገት መፋጠን የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዲጂታል መታወቂያ እየሰራች ያለው ስራ ከአፍሪካ ትልቁ መሆኑን አንስተው፤ በመጪው ሳምንት በሚጀመረው አይዲ-4 አፍሪካ ኤክስፖ ላይ በቀጣይ የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል ብለዋል።
በኤክስፖው ከተሳተፉት መካከል ከአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የዌብና አፕሊኬሽን ቲም ሊደር ደጀኔ ሀብቴ እንደገለጹት፤ በኤክስፖው በክልሉ አገልግሎት ላይ የዋሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጤቶች ቀርበዋል፡፡
በተለይ በኮሪደር ልማት የተሰሩ ስራዎች እና መሰረተ ልማቶቹን ተከትሎ የተገጠሙ ዲጂታል ካሜራዎች እንዲሁም የስማርት ሩም ቴክኖሎጂዎችን ማቅረባቸውን አንስተዋል፡፡
በኤክስፖው በአማራ ክልል በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ማሳየት መቻላቸውን አመልክተው፤ በተለይ በተለያዩ የአገሪቷ ክልሎች የተከናወኑ ውጤታማ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስራዎች መመልከታቸውንም ገልጸዋል።
በክልሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ልምድ መቅሰማቸውን ጠቅሰው፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለማፋጠን እንተጋለን ብለዋል፡፡
በሶፍትዌር ማልማት ላይ የተሰማራ ሀገር በቀል የግል ድርጅትን በኤክስፖው ይዘው የቀረቡት መኮንን ትኩ በበኩላቸው፥ ኤክስፖው ኢትዮጵያ በዲጂታል ልማት የደረሰችበትን ከፍታ ያሳየ ነው ብለዋል።
መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ተከትሎ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ ለተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችም ትልቅ ድጋፍና ትኩረት መሰጠቱን ጨምረው አንስተዋል።
ተሳታፊዎቹ የዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታን ለማፋጠን በዘርፉ እያከናወኑ ያሉትን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025