ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 8/2017 (ኢዜአ)፦የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ውጤቶችን ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ በማድረግ ወደ ተግባር ተለውጠው የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እንዲያጎለብቱ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ዩኒቨርሲቲው በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ በሚችሉ ጥናታዊ ምርምሮች ላይ አተኩሮ እንደሚሰራም ተገልጿል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ''ተግባር ተኮር ምርምር እና ፈጠራ ስራዎች ለዘላቂ ልማት'' በሚል መሪ ሃሳብ 13ኛ ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሄዷል።
የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዘውድነህ ቶማስ (ዶ/ር) በወቅቱ ለኢዜአ እንዳሉት፥ ዩኒቨርሲቲው የምርምር ውጤቶችን ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ በማድረግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እንዲያጎለብቱ እየሰራ ነው።
በተጨማሪም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለሚያጠናክሩ የምርምር ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል።
የምርምር ስራዎቹም በአካባቢው የሚካሄዱ የእርሻና የእንስሳት ልማት ስራዎችን በማዘመን በሽታንና የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም አርሶ አደሩን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው የተካሄደው የምርምር ኮንፈረንስም የተጠቀሱትን ጨምሮ ሌሎች የምርምር ውጤቶችን ለፖሊሲ አውጪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሚጠቅም መልኩ ለማዘጋጀትም እገዛው የጎላ እንደሆነም አንስተዋል።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም በበኩላቸው፥ ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው በሚሰራቸው ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች የላቀ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።
በተለይም በኢኮኖሚው ዘርፍ ግብርናን ማዘመን የሚያስችሉ ምርምሮችና በማህበራዊ መስክም በትምህርትና ጤና ረገድ የማህበረሰቡን ህይወት የሚለውጡ ስራዎች መስራቱን አብራርተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025