ቡኖ በደሌ፤ ግንቦት 9/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በመኸር ወቅት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ የግብርና ግብዓቶች እየቀረቡ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ግብርና ቢሮ የስራ ሀላፊዎች በቡኖ በደሌ ዞን የመኸር እርሻ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።
በዚሁ ጊዜ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ እንደገለጹት በክልሉ በመኸር እርሻ ምርትና ምርታማነትን ለማሳድግ ግብዓት በስፋት እየቀረበ ነው።
በክልሉ በዘንድሮ የመኸር እርሻ 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ አስፈላጊ ግብዓቶች እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።
ለመኸር አዝመራ ከሚያስፈለገው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን ከስድስት ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ወደ ክልሉ መድረሱን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚሆነው አርሶ አደሩ እጅ ደርሷል ብለዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ በአፈር አሲዳማነት የተጠቃ መሬትን በተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማከም አበረታች ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ ቡኖ በደሌ ዞን ዳቦ ሃና ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አሸናፊ ጸጋዬ፤ ለመኸር እርሻ መሬታቸውን በትራክተር በማረስ እያዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በጋ ላይ ስንዴ በክላስተር አርሰው የተሻለ ምርት ያገኙበት ማሳቸውን አሁን ደግሞ በመኸር እርሻ በቆሎ ለማልማት እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል።
ሌላው አርሶ አደር ኦበሳ ዳባሳ፤ በአቅራቢያቸው ካሉ ሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በመሆን መሬታቸውን በክላስተር ለማልማት እያረሱና ለመዝራት እየተዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ተቀናጅተን በክላስተር ማልማታችን የተሻለ ምርት ለማግኘት ያስችለናል ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025