አዲስ አበባ፤ግንቦት 10/2017 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የኮሪደር ልማት ስፍራዎች ለወጣቱ አማራጭ የመዝናኛ ስፍራ ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙ ኢዜአ ያነጋገራቸው ወጣቶች ገለፁ።
በአዲስ አበባ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁና በግንባታ ሂደት የሚገኙ የኮሪደር ልማትና የመልሶ ግንባታ ተግባራት መዲናዋን ውብ ገጽታ በማላበስ ለነዋሪዎቿ ምቹ የኑሮ ምኅዳርን ፈጥረዋል።
አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ የከተማ ተወዳዳሪነት አቅምን በመፍጠር ከኢትዮጵዊያን ባሻገር የአፍሪካ መዲናነቷን እንድታስጠብቅ ወሳኝ ዕድል ፈጥሮላታል።
በአዲስ አበባ ከተማ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁና በግንባታ ሂደት የሚገኙ የኮሪደር ልማትና የመልሶ ግንባታ ተግባራት አስመልክቶም ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ወጣቶች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹም፤ መዲናዋን ውብ ገጽታ ያላበሷትና ምቹ የከተሜነት ምኅዳር እያጎናጸፏት የሚገኙ የኮሪደርና መልሶ ግንባታ ስራዎች የወጣቱን ፍላጎትና መሻት ታሳቢ ያደረጉ ናቸው።
ወጣት እስራኤል ዳንኤል እንደሚለውም፤ በካዛንችስና አካባቢው በአጭር ጊዜ ውስጥ ፍጥነትን ከጥራት ያዋሃዱ አኩሪ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ታዝቧል።
በአጭር ጊዜ በጥራትና ፍጥነት ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ፕሮጀክቶችም አካባቢውን ወብ ገጽታ በማላበስ ለመዲናዋ ነዋሪዎች ማራኪና አማራጭ የመዝናኛ ቦታ መፍጠራቸውን ተናግሯል።
መዲናዋን ውብ ገጽታ ያላበሷት የኮሪደር ልማት ስራዎችን መጎብኘት በስራ የደከመን መንፈስ የሚያበረቱ ናቸው ያለው ደግሞ ከሳሪስ አካባቢ ለመዝናናት እንደመጣ የገለጸው ወጣት ደሳለኝ ይፍረደው ነው።
በብዙ መልኩ ውብ ገጽታን የተላበሱት የካዛንችስና አቧሬ አካባቢዎችም የነበራቸውን የደበዘዘ ገጽታ በመቀየር ለመዲናዋ ወጣቶች በአማራጭ የመዝናኛ ስፋራነት እያገለገሏቸው እንደሚገኝ ገልጿል።
አቧሬ አካባቢ እንደምትኖር የገለጸችው ሶፍያ መሃመድም እንዲሁ፤ የካዛንችስ ኮሪደር ልማት በጥራትና ፍጥነት ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃቱ አግራሞትን ፈጥሮብኛል ብላለች።
በአካባቢው የተደረገው ውብና ማራኪ የልማት ስራም ህፃናት እንዳሻቸው ቦርቀው እንዲጫዎቱ፤ ወጣችም ሃሳባቸውን በጥሞና እንዲቀያየሩ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
እንደ ወይዘሮ ዘነበች አተዎ ገለፃ፤ በካዛንችስና አካባቢው የተደረገው ሁለንተናዊ ለውጥ ማራኪ ስፋራን በመፍጠር ለመዲናዋ ወጣቶች ድንቅ የመዝናኛ ቦታ ለመሆን ችሏል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ከተማዋን ውብ ገጽታ ያላበሷት የልማት ፕሮጀክቶች የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለነዋሪዎች ምቹ የኑሮ ከባቢ መፈጠሩን አንስተዋል።
የመዲናዋ ነዋሪዎችም በጥራትና ፍጥነት ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ማራኪ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ነው አጽንኦት የሰጡት።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025