አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ልምዷን የምታካፍልበት አይዲ 4 አፍሪካ ጉባኤን ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደምታስተናግድ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ።
ከ100 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት አይዲ 4 አፍሪካ ጉባኤ በዲጂታል ማንነት ላይ የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግበት ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ተደርጎ በነበረው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው ለአዘጋጅነት የተመረጠችው።
ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዲጂታል ማንነትን ለማረጋገጥ ያደረገችው ጥረትና የመንግስት ቁርጠኝነት የዘንድሮውን ጉባኤ በአዘጋጅነት እንድትመረጥ ማስቻሉም በወቅቱ ተገልጿል።
በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላት ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ለኢዜአ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው።
ባለፈው ዓመት በተካሄደው ፎረም በተለይም ከስደተኞች ጋር ተያይዞ ያከናወነቻቸው ተግባራት ለበርካታ ሀገራት በተሞክሮነት ተወስዷል ብለዋል።
ነገ በይፋ በሚከፈተው አለም አቀፍ ጉባኤ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙና በዲጂታል ማንነት ዙሪያ ልምድ ልውውጥ አንደሚካሄድም ጠቁመዋል።
ባለፉት 2 ዓመታት ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፤ ከ50 በላይ ተቋማት ዲጂታል መታወቂያን በሲስተማቸው አካተው አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል።
ይህም በተለይ ደህንነቱ የተረጋገጠ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ አገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍና የዜጎችን እርካታ ለመጨመር እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ዲጂታል ማንነት ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር የጀመረቻቸው ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑንም አንስተዋል።
ፋይዳ በሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት፣ ለፋይናንስ ዘርፉና ለሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምቹ መደላድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።
ለሌሎች ሀገራት በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያም ከሀገራት ልምድ ትቀስማለች ብለዋል።
ነገ በሚጀመረው አይዲ 4 አፍሪካ አለም አቀፍ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የተለያዩ ሀገራት በዲጂታል ማንነት ላይ ያከናወኗቸውን ስራዎች ከማቅረብ ባለፈ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025