የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለኢትዮጵያ የሁሉን አቀፍ ዕድገትና የዘመናዊነት ጉዞ ሁነኛ ማሳያ ነው

May 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦ ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ ለኢትዮጵያ የሁሉን አቀፍ ዕድገትና የዘመናዊነት ጉዞ ስኬት ሁነኛ ማሳያ መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሔ አርአያሥላሴ ገለጹ፡፡

ዲጂታል ማንነት ላይ ያተኮረው አይዲ 4 አፍሪካ ዓመታዊ ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ከ105 ሀገራት የመጡ ተወካዮችን ጨምሮ ከ2 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።


በጉባኤው ኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ወይም ፋይዳ ስርዓትን በስኬታማነት ተግባራዊ እያደረገች መሆኗ ተገልጿል።

ፋይዳ ለኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ወሳኝ የሆነ የዲጂታል መሰረተ ልማት መገንባት ላይ ያተኮረ ነውም ተብሏል፡፡

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሔ አርአያሥላሴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ 15 ሚሊየን ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ፋይዳ ዲጂታል ኢትዮጵያን የመገንባት ጉዞ አካል መሆኑን አንስተው ለኢትዮጵያ መጻኢ ዕድል መሠረት ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እያስመዘገበች ለምትገኘው ስኬት የመንግሥት ቁርጠኝነት፣ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ ኢትዮጵያ እያደረገች ለምትገኘው ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሳካት ጉልህ አበርክቶ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ዕድገትና የዘመናዊነት ጉዞ ስኬት ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑንም ጨምረው ጠቁመዋል፡፡

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ተግባራዊ በሆነባቸው ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ይወስድ የነበረውን ጊዜ እስከ 60 በመቶ መቀነስ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

የዲጂታል መታወቂያው በመንግስትም ይሁን በግል ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ለተደራሽነት ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.