የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በሚደረገው ጥረት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሚና መጠናከር አለበት - ቢሮው

May 28, 2025

IDOPRESS

ባህር ዳር፤ ግንቦት 19/2017(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በጀትን ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በሚደረገው ጥረት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሚና መጠናከር እንዳለበት የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው በመንግስት የፋይናንስ አስተዳደርና በፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ዛሬ ሰጥቷል።

የቢሮው ኃላፊ ጥላሁን መኃሪ(ዶ/ር) በመድረኩ እንደገለፁት በክልሉ የተመደበውን በጀት ለታለመለት ዓላማ መዋል አለመዋሉን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሚና ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።


ይህም ውስን የሆነውን የህዝብ ሃብት ለክልሉ እድገት በማዋል የህብረተሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ነው የገለጹት።

በክልሉ የሚበጀተውን በጀት ህብረተሰቡ የማወቅ መብት አለው ያሉት የቢሮ ኃላፊው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉም የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ኃላፊነቱን ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል።


በመድረኩ የተሳተፉት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስቻለ አየሁዓለም እንደገለጹት በጀት የልማት ስራዎች ማሳለጫ ቁልፍ መሳሪያ ነው።

ለልማቱ የሚመደብን ውስን በጀት ለታለመለት ተግባር እንዲውል የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ህብረተሰቡን የማስገንዘብና የማሳወቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

አሚኮ በጉዳዩ ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በኩል የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም አረጋግጠዋል።


የክልሉ መንገድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በትግሉ ተስፋሁን በበኩላቸው በመድረኩ ስለፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ያገኙትን ግንዛቤም በተቋማቸው የሚከናወኑ የመንገድ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲከናወኑ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

ለአንድ ቀን በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናም ከክልሉ ቢሮዎችና ከተለያዩ የሚዲያ አካላት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.