ጋምቤላ ፤ግንቦት 20/2017 (ኢዜአ)፡- የዲጂታል መሰረተ ልማትና የሰው ኃይል ልማትን በማጠናከር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ከጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ጋር በመሆን በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት የተገነባውን የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍል መርቀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የዲጂታል መሰረተ ልማት እንደ ሀገር ለታለመው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የዲጂታል መሰረተ ልማት በተለይም የሰው ኃይል ልማቱን በማሳለጥ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ዓይነተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም የዲጂታል መሰረተ ልማትና የሰው ኃይል ልማትን በማጠናከር የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማፋጠን የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
የስማርት ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂው የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለማሳለጥ የሚያስችል ስለመሆኑም አስረድተዋል።
ሚኒስቴሩ ከክልሎች ጋር በመተባበር በዕለቱ የተመረቀውን የዲጂታል ኮሙኒኬሽን ስማርት ክፍል ያስገነባው የክልሎችን ፍትሐዊ ተጠቀሚነት ለማረጋገጥ በማለም መሆኑንም ገልጸዋል።
የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው የዲጂታል መሰረተ ልማት የታለመውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ ለማሳለጥ የጎላ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
የዲጅታል መሰረተ ልማት እየተካሄዱ ለሚገኙት የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መሳለጥ የጎላ አበርክቶ እንዳለው አንስተው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በክልሉ ላስገነባው የስማርት ኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት አመስግነዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025