ባህርዳር ፤ ግንቦት 22/2017 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በእርሻ ኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ባለሃብቶች 11ሺህ 267 ሄክታር መሬት ተለይቶ መዘጋጀቱን የክልሉ መሬት ቢሮ አስታወቀ።
በቢሮው የገጠር መሬት ኢንቨስትመንት ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ በላይ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች መሬት ተለይቶ የተዘጋጀው በ10 ዞኖች ውስጥ ነው።
ለእርሻ ኢንቨስትመንት እንዲውል ተለይቶ ከተዘጋጀው 11 ሺህ 267 መሬት ከ2 ሺህ ሄክታር የሚበልጠው ቀደም ሲል የመስሪያ ቦታ ጠይቀው ሲጠባበቁ ለቆዩ 20 ባለሃብቶች መተላለፉን ተናግረዋል።
እነዚሀ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ በመውሰድ እያንዳንዳቸው ከ20 እስከ 100 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ቀሪው ከዘጠኝ ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቀጣይ ለሚቀርቡ ባለሃብቶች ለማስተላለፍም አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ባለሃብቶቹ የሚያቀርቡት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ተገምግሞ አሸናፊ ለሚሆኑት መሬቱን ፈጥኖ በማስረከብ ወደልማት እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ባለሃብቶቹ ወደስራ ሲሰማሩም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩም አቶ ጥጋቡ አስታውቀዋል።
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩት አቶ መስፍን ክፍሉ በሰጡት አስተያየት፤ በወሰዱት መሬት ላይ እያለሙ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም በ2017/2018 የምርት ዘመንም የበቆሎ ዘር ለማባዛት በአሁኑ ወቅት መሬቱን አለስልሰው ማጠናቀቃቸውን ጠቅሰዋል።
ቀደም ሲልም በተለይ ለአካባቢው አርሶ አደር የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ማሾ፣ ቲማቲምና ሽንኩርት በማልማት ውጤታማ እንደሆኑም አውስተዋል።
ለበርካታ ዜጎችም የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቁመዋል።
ባለፉት ዓመታት በክልሉ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ አንድ ሺህ 638 ባለሃብቶች በተረከቡት 203 ሺህ 858 ሄክታር መሬት ላይ እያለሙ መሆኑን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025