አርባ ምንጭ፤ ግንቦት 25/2017(ኢዜአ)፦ በየደረጃው ያለው አመራር ለህዝብ ጥያቄዎች ወቅቱን የዋጀ ምላሽ ለመስጠት በአመራር ጥበብ መታገዝ እንዳለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።
በፐብሊክ ኢንተርፕርነርሽፕ እና ኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ አመራሩ እያደገ ለመጣው የህዝብ ተለዋዋጭ ጥያቄ ወቅቱን የዋጀ ምላሽ ለመስጠት በአመራር ጥበብ ታግዞ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።
የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባውም አመልክተዋል።
የለውጡ መንግስት ዘመኑን በሚዋጅ እይታ በመንቀሳቀስና ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በሁለንተናዊ የልማት ዘርፎች ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ሲሉም አክለዋል።
እየተስተዋሉ ላሉ ተደራራቢና ተለዋዋጭ ክስተቶች ተገቢ ምላሽ ለመስጠት መንግስት ፈጠራና ፍጥነት የታከለበት ተግባር እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ክልሉን የሰላም፣ የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ከተለመደው አሰራር በመውጣት በፈጠራና በፍጥነት የታከለ የኢንተርፕርነርሽፕ እና ኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለመፍጠር እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የፌዴራል ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን(ዶ/ር) እንዳሉት የፐብሊክ ኢንተርፕርነርሽፕ እና ኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ለአመራሩ የሚሰጠው ስልጠና የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን የሚያግዝ ነው።
አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ፈጣን ለውጥ እንዲመጣ ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸውም ጨምረው ጠቅሰዋል።
በየደረጃው ያለው አመራር በፈጠራና በፍጥነት የታከለ ለውጥ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት እንዲችልና ለዚህም ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር ታስቦ መድረኩ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው ስልጠና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በስሩ ባሉ 12 ዞኖች የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025