አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን በማድረግ ሂደት ባለሃብቶች ሚናቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የገቢዎች ሚኒስቴር "ለሁለንተናዊ ብልፅግና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ምክክር አካሂደዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ባለሃብቶች ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡
በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት በተደረገው ሀገራዊ ሪፎርም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ መስኮች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ የተመዘገቡት ስኬቶች ባለሀብቶች መንግስት ለንግድና ኢንቨስትመንት የፈጠረውን ምቹ ከባቢ ወደ ተግባር በመቀየር መሆኑን አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለተመዘገበው ስኬት ባለሃብቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው በመግለጽ፤ መንግስት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ተቋቁሞ ያመጣው ውጤት መሆኑ መዘንጋት የለበትም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ሁኔታዎችና ሌሎች ፈተናዎችን ወደ እድል እየቀየረች የማንሰራራት ጉዞ ላይ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ባለሃብቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ባለሀብቶች ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል፡፡
መንግስት ለሰላም የሚያደርገውን ጥረት መደገፍ እንደሚገባም ነው ሚኒስትሩ ጨምረው የተናገሩት፡፡
የመንግስት ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ባለሃብቶች ደግሞ ለስኬታማነቱ ቅርብ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ባለሀብቶች ከኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እርሾ በመውሰድና መንግስት የፈጠረውን ምቹ ዕድል በመጠቀም ስራ መፍጠር፣ ምርታማነትን መጨመር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025