አዲስ አበባ፤ግንቦት 28/2017(ኢዜአ)፦የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከኢትዮጵያ ሁኔታ የተነሳ ከሌሎች የተማረና በኛ ልክ የተሰፋ ሪፎርም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም መነሻ ራስን ከማየት የጀመረ መሆኑን አመልክተዋል።
በኢኮኖሚው ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር መጠነ ሰፊ ውይይቶች ማድረጉን አስታውሰዋል።
በኢኮኖሚ ፈተና ውስጥ ሆነው ወደ ሪፎርም በመሸጋገር ለውጥ ካመጡ ሀገራት ተሞክዎች መወሰዳቸውንም እንዲሁ።
በውይይቶቹ እና ተሞክሮ በመቅሰም የተገኙ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ወደ ተግባር መግባቱን አንስተዋል።
በሪፎርሙ አማካኝነትም በኢኮኖሚው ላይ የሚታዩ ለውጦች መመዝገባቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሀገር በቀል ነው ሲባል ከሌሎች አንማርም ዝግ ነን ማለት እንዳልሆነ ሊሰመርበት እንደሚገባ አመልክተዋል።
የኢኮኖሚ ሪፎርሙም ለሙሉ ለሙሉ ከውጭ የተቀዳ የሚለው አስተያየት ተገቢ እንዳልሆነም ነው ያነሱት።
ከኢትዮጵያ የውጭ እዳ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ዓለም ባንክ እና ሌሎች አበዳሪዎች ጋር የተደረጉ ድርድሮች የሀገሪቷን ጥቅም እና ፍላጎት ያስጠበቁ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከኢትዮጵያ ሁኔታ የተነሳ ፣ ከሌሎች የተማረ፣ በኛ ልክ የተሰፋ ሪፎርም መሆኑ ውጤት እንደተገኘበት አንስተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025