አዲስ አበባ፤ግንቦት 30/2017 (ኢዜአ)፦የኮሪደር ልማቱ ስነ-ውበትን የገለጠ፣የተደበቁ ሃብቶችን ጥቅም ላይ ያዋለ እና የሰዎችን ህይወት ያሻሻለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እየለሙ ያሉ የኮሪደር ልማቶች ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው ባሻገር የጤና ጠቀሜታ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ንጽህናው ባልተጠበቀ አካባቢ የሚኖር ማንኛውም ማህበረሰብ የጤናው ሁኔታ አደጋ ውስጥ መውደቁ አይቀርም ነው ያሉት፡፡
በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች የኮሪደር ልማት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ከዚህ በፊት ዝናብ በጣለ ቁጥር አይደለም ለመኖር አልፎ ለመሔድም ከባድ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በተከናወኑ ሰፊ የልማት ስራዎች ከተማዋ ለጤና፣ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እጅግ የምትመች አስደማሚ ከተማ እየሆነች መጥታለች ነው ያሉት፡፡
ከመንገድ አኳያም የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶች ተለይተው በመሰራታቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴው የተሳለጠ እንዲሆንና የአደጋዎች ምጣኔ እየቀነሰ እንዲመጣ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት በሰው ሀገር አይተን የምንቀናባቸውን የልማት ስራዎች አሁን ላይ በሀገራችን ተተግብረው እየታዩ መሆኑን አመልክተው፤ የወንዝ ዳር ልማቶችም ውበትን የገለጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ስነ-ውበትን የገለጠ፣ የተደበቁ ሃብቶችን ጥቅም ላይ ያዋለ እና የእያንዳንዱን ሰው ህይወት ያሻሻለ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ከተሜነት በፍጥነት እያደገ እንደሚሔድ ጥናቶችን ዋቢ አድርገው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሰው ቁጥር እያደገ በመጣ ቁጥር ደግሞ የከተማ መሰረተ ልማቶችን ማሳደግ ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን አብራርተዋል።
በቀጣይም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማትና ሌሎች ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
#ኢዜአ #Ethiopia #Ethiopian_News_Agency
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025