የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ሥራ ፈጣሪዎች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር መቀየር የሚችሉበት ምቹ ስነ ምህዳር መፍጠር ተችሏል

Jul 1, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 22/2017(ኢዜአ)፦ሥራ ፈጣሪዎች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር መቀየር የሚችሉበት ምቹ ስነ ምህዳር መፍጠር መቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለፁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የፈጠራ ሀሳብ በማቅረብ ስታርት አፕ ለመጀመር እየተደረገ ያለውን ዝግጅት በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ የፈጠራ ሥራዎች ለአንድ ሀገር እድገት መሰረት በመሆናቸው ዘመኑን የዋጁ የፈጠራና የምርምር ሥራዎች ማስፋት ያስፈልጋል።

ወጣቶች በፈጠራና ምርምር ሥራዎች እንዲሳተፉ ትኩረት መደረጉን አንስተው፤ ለውጤታማነቱም አስቻይና የጎለበተ ምህዳር መፍጠር እንደሚገባ አንስተዋል።

ስታርት አፕ በዋነኝነት የወጣቶችን ሃሳብ መሰረት ያደረገ የፈጠራ ስራ ውጤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ሃሳብን ወደ ተግባር መለወጥ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የአንድ ሀገር እድገት እና ብልፅግና መሠረት የሚያደርገው ጥራት ባለው በፈጠራ ሥራ ውጤቶች በመሆኑ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በዚህም የፈጠራ ስራ ውጤት ለሆነው ስታርት አፕ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ሕጋዊ አሰራሮችን በመዘርጋት ምቹ ምህዳር ለመፍጠር ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ የፈጠራ ሥራ ሃሳባቸውን መቀየር የሚያስችል ምቹ ምህዳር መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።

የግል ዘርፉ በስታርታ አፕ እና ሌሎች የፈጠራ ሥራዎች እንዲሳተፍ የዘርፉ ምህዳር እንዲሰፋ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ተቋማት ለችግር ፈቺ የምርምርና ኢኖቬሽን ሥራዎች መጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

ስታርት አፕ ለኢትዮጵያ አዲስ እንደመሆኑ በርካታ ወጣቶች ወደ ዘርፉ የመግባት ፍላጎቶች እየጨመረ መሆኑን አንስተው፤ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አንዱ የህግ ማእቀፍ በመሆኑ በሂደት ላይ ነው ብለዋል።

የህግ ማዕቀፉ ፀድቆ ወደ ተግባር ሲገባ አጠቃላይ የስታርት አፕ ስነ ምህዳሩን የሚያጎለብትና የፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ወጣቶች ተስፋን የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል።

በዘርፉ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለስታርት አፕ ልዩ ትኩረት መሰጠቱና ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም አድንቀዋል።

ወጣት ናትናኤል አዳነ በበኩሉ አገልግሎት የሰጡ የፕላስቲክ ቁሳቁሶችን መልሶ በመጠቀም የኮንስትራክሽን ግብዓት የሆኑ ምርቶች ማምረት ላይ መሰማራቱን ተናግሯል።


መንግስት ባደረገለት የገንዘብ እና ሌሎች ድጋፎች ፈጥኖ ወደ ስራ ለመግባት እንዳስቻለው ተናግሯል።

ወጣት ሳሙኤል ዘነበ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ የጤና አገልግሎት ላይ ተሰማርቶ በአዲስ አበባ ውጤታማ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፆ፤ በቀጣይ ስራውን ወደ ተለያዩ ክልሎች አስፍቶ ለመስራት ማቀዱን ተናግሯል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.