🔇Unmute
ሀዋሳ፤ መስከረም 19/2018 (ኢዜአ) :- በሲዳማ ክልል በዘንድሮው በጋ ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ እንደሚለማ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ ።
በሲዳማ ክልል የ2018 የምርት ዘመን የበጋ መስኖ ልማት የንቅናቄ መድረክ ተካሄዷል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ እንደገለፁት በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ገበያን ለማረጋጋት ለመስኖ ልማት ሥራ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
ይህም ባለፉት ዓመታት በመስኖ የሚለማ መሬት ሽፋንን በማሳደግ የምርት መጠን እንዲጨምር መደረጉን ገልፀዋል፡፡
ለአብነትም ባለፈው ዓመት በበጋ መስኖ 73 ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት እንደተቻለ ጠቅሰው ይህንንም በዘንድሮው በጋ ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማሳደግ መታቀዱን ጠቁመዋል ።
አርሶ አደሩ የመስኖ አውታሮችን ለማልማት ኩሬዎችን፣ አነስተኛ ጉድጓዶችን፣ ጅረቶችንና ወንዞችን ጨምሮ ሁሉንም የውሃ አማራጭ ተጠቅሞ በማልማት ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት እንዲችል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡
የክልሉ መንግስት ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ በጀት በመመደብና ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን በመቆፈር ከዚህ ቀደም በመስኖ ልማት የማይታወቁ አካባቢዎች ጭምር ዓመቱን ሙሉ እንዲያመርቱ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የቢሮው ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባንጉ በቀለ በበጋ የመስኖ ልማት ከ80 ሺህ 55 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ18 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን አስረድተዋል፡፡
ከመስኖ ልማቱም ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬት በኩታ ገጠም የሚለማ መሆኑን ጠቁመው በዚህ የልማት ሥራም ከ350 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል፡፡
ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያ እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ ለአርሶ አደሩ እንዲደርሱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በንቅናቄ መድረኩ ላይም የክልሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025