የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ተደርጎ  የተጀመረው የዲፕሎማሲ ጥረት የሚደነቅ ነው- ምሁራን

Oct 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

መስከረም ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ተደርጎ ይህንኑ ለማሳካት የተጀመረው የዲፕሎማሲ ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በኦዳ ቡልቱም ምሁራን ገለጹ፡፡

የባህር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ የህልውና ጉዳይ ነው በማለት መንግስት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ እያከናወነ ይገኛል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ኢዜአ ያነጋገራቸው ምሁራን የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ተደርጎ ለማሳካት የተጀመረው የዲፕሎማሲ ጥረት የሚደነቅ ስለመሆኑ አንስተዋል።

በዩኒቨርሲቲው የህግ ትምህርት ቤት መምህር መሀዲ የሱፍ፤ በባህር በር ጉዳይ መንግስት በቁጭት በመነሳት ኢትዮጵያ ተቆልፋ መኖር አትችልም በማለት የባህር በር ባለቤት ልትሆን ይገባል ብሎ የያዘው አቋም የሚደገፍ መሆኑን ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ከባህር በር ተነጥላ ለከፍተኛ ወጭና እንግልት እንዲሁም ከባህር ለሚነሱ የጸጥታ ስጋቶች ተጋልጣ መቆየቷ ተገቢነት የሌለው መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ መንግስት የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ተደርጎ ለማሳካት የጀመረው የዲፕሎማሲ ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ሌላኛው የዩኒቨርሲቲው መምህር ደመቀ ሲማ፤ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዓለም አቀፍ አጀንዳ በማድረግ መንግስት የሄደበትን የዲፕሎማሲ ርቀትና ያላሰለሰ ጥረት አድንቀዋል።


በአለም አቀፍ የባህር ህግ መሰረት የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ተፈጥሯዊ እና ህጋዊ መብት በመሆኑ ምላሽ እንደሚያገኝም ጽኑ እምነት አለኝ ብለዋል።፡

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከሰሞኑ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ ያላትን መብት ለማስከበር የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል መናገራቸው መንግስት በጉዳዩ ላይ ጠንካራ አቋም ይዞ መቀጠሉን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑም አንስተዋል።

ሌላኛው የዩኒቨርሲቲው መምህር አብዱራህማን ኢብራሂም በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ያስመዘገበው ዲፕሎማሲያዊ ድል እና በቀይ ባህር ላይ ያለውን መብት ለማስከበር የጀመረው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።


የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በኢትዮጵያ ላይ በቀጥታ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ከማሳረፍ ባለፈ መረጋጋት እንዳይኖር በውስጥ ባንዳዎች ብዙ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተው በጋራ ቆመን መመከት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋለ።

ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ የራሷን የጦር ሰፈር በማደራጀት ጠንካራ የባህር ኃይል ብትገነባ ከራሷ ባለፈ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ሚናዋ የላቀ እንደሚሆንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.