የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ሸማቾች ከቅዳሜና እሁድ የገበያ አማራጮች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ ነው

Oct 27, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፦ ከቅዳሜና እሁድ የገበያ አማራጮች መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ሸማቾች ተናገሩ።

የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና ገበያን ለማረጋጋት የቅዳሜና እሁድ የገበያ አማራጮች ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው።

በእነዚህ ገበያዎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ቀጥታ ከአምራቹ ወደ ሸማቹ እየቀረቡ ይገኛሉ።

ይህም ሸማቹ የሚፈልጋቸውን ምርቶች በቀላሉ እንዲያገኝ ዕድል ፈጥሯል።

ኢዜአ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች ላይ ባደረገው ቅኝትም ይህን ማረጋገጥ ችሏል።

በቅዳሜ ገበያ ግብይት ሲፈጽሙ ካገኘናቸው መካከል ማርታ ዳምጠው አንዷ ናቸው።


እርሳቸው እንደሚሉት፤ በቅዳሜና እሁድ ገበያ የሚቀርቡ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች የሸማቹን ፍላጎትና የመግዛት አቅም ያማከሉ ናቸው።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ታምሩ አያና የቅዳሜና እሁድ ገበያ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ዕድል የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸው፤ ገበያው በሁሉም አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።


የቅዳሜና እሁድ ገበያ መሰረታዊ ሸቀጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ያስቻላቸው መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ ሀብታሙ አጎናፍር ናቸው።


ነጋዴዎች በበኩላቸው፤ ጥራት ያላችው መሰረታዊ ምርቶችን በብዛትና በበቂ መጠን እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.