🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፡-በኢትዮጵያ የሚከናወኑ ሜጋ ፕሮጀክቶች በታለመላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መንግስት በልዩ ክትትልና ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሔደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት የግንባታ ሒደት ላይ ያሉና መሰረት የተቀመጠላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የሀገርን ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ፕሮጀክቶች እውን ሆነዋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ በተካሔደው ሀገራዊ ሪፎርም የማዕድን ሀብትን አሟጦ መጠቀም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተግባራዊ መደረጉን አንስተው የጋዝ፣ የነዳጅና ሌሎች ማዕድናትን ወደ ጥቅም የሚቀይሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች መጀመራቸውን ተናግረዋል።
የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ማምረትና መጠቀም የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ ከዳንጎቴ ጋር በመተባበር ወደ ግንባታ መግባቱን ገልጸው፥ ይህም የኢትዮጵያን አርሶ አደሮች የብዙ ዘመናት ችግር የሚፈታ ነው ብለዋል።
በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችለው ግዙፉ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የዲዛይን ስራ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው ኢትዮጵያን የአፍሪካ አቪየሽን ማዕከል የሚያደርጋት መሆኑን ተናግረው፥ ለ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ መጠናቀቅ መንግሥት በልዩ ትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025