🔇Unmute
ሮቤ ፤ ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ)፡-በባሌ ዞን በግብይት ውስጥ ህገወጥ ተግባር የፈጸሙ 1 ሺህ 704 ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ንግድ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ ሙሲና አብደላ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በዞኑ ከመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ በምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላትን ለይቶ ለመቆጣጠር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ነው።

በዞኑ አስር ወረዳዎች የተቋቋመው ግብረ ሃይል 9 ሺህ 900 በሚጠጉ ነጋዴዎች ላይ ባደረገው የቁጥጥርና ክትትል ስራ 1 ሺህ 705 የሚሆኑ ነጋዴዎች ሕግ ተላልፈው መገኘታቸውን አመልክተዋል።

በግብረ ሀይሉ ከተለዩት ሕገ ወጥ ተግባራት መካከል የንግዱ ማሀበረሰብ በሚያቀርበው ምርት ላይ የዋጋ ዝርዝር አለመለጠፍ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ፣ ግልፅ መረጃ ለሸማቹ አለመስጠት እንደሚገኙበት አንስተዋል።
በዚህም ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ፈጽመው በተገኙ 1 ሺህ 704 ነጋዴዎች በሚያንቀሳቅሱት የንግድ ድርጅቶች ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣የማሸግና ሌሎች አስተዳደራዊ እርምጃዎች መወሰዱን አስታውቀዋል።

ከሕገ ወጥ ተግባራቸው በማይመለሱ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፈቃድ እገዳና እስከ መሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ምርትን በመደበቅና ያለአግባብ ዋጋ በመጨመር ድርጊት ላይ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶችን በመጠቆም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በሮቤ ከተማ ነዋሪ ወጣት ሲፈን ግርማ በሰጠችው አስተያየት፤ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት በመንግስት እየተሰራ ያለው ተግባር ገበያው እንዲረጋጋ በማድረጉ ይሄው ተግባር እንዲቀጥል ጠይቃለች።

ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የተጀመረው የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹት ደግሞ ወይዘሮ መሰረት አድማሱ ናቸው።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026