የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የሐረሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር፤ህዳር 2/2018 (ኢዜአ)፦የሐረሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የሐረሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢፌዴሪ ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አልማዝ መሰለ በተገኙበት ነው ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው።


በከተማው የተገነባው ማዕከሉ በመጀመሪያ ምዕራፍ በሰባት ተቋማት 22 አገልግሎቶችን አቀናጅቶ የሚሰጥ መሆኑም ታውቋል።

የሐረሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እነዚህን አገልግሎቶች በተቀናጀ መንገድ መስጠት በሚያስችል መልኩ በሰው ሃይልና በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ ወደ ስራ መግባቱ ነው የተገለጸው።

በመርሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪና የኢፌዴሪ ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አልማዝ መሰለን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.