🔇Unmute
ደብረ ማርቆስ ፤ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፡- በምስራቅ ጎጃም ዞን በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ኪሎ ግራም በላይ የማር ምርት ማምረት መቻሉን የዞኑ እንስሳትና አሳ ሃብት መምሪያ ገለጸ።
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሌማት ትሩፋት እና ሌሎችም ኢንሸቲቮች ተግባራዊ እየተደረጉ ውጤትም እየተመዘገበባቸው ይገኛል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን እንስሳትና አሳ ሃብት መምሪያ የንብና ሃር ልማት ባለሙያ አቶ ስማቸው ዳምጤ ለኢዜአ እንደገለጹት፤በዞኑ ከሰብል ልማት ጎን ለጎን የአካባቢውን ምቹነት በመጠቀም የንብ ማነብ ስራ በብዛትና በስፋት እየተከናወነ እና ውጤትም እየተገኘ ነው፡፡
በዚህም መሰረት በተያዘው በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ አንድ ሚሊየን ኪሎ ግራም በላይ የማር ምርት ለማምረት ታቅዶ እስካሁን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ኪሎ ግራም በላይ ማምረት መቻሉን ገልጸዋል።
በዘርፉ ልማት አሁን ላይ ከ11 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በተደራጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑን አንስተው በዚህም ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከአንድ ዘመናዊ ቀፎ በአማካይ 30 ኪሎ ግራም፣ ከሽግግር ቀፎ 18 ኪሎ ግራም ከባህላዊ ቀፎ ደግሞ 8 ኪሎ ግራም የማር ምርት እየተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
በዞኑ አዋበል ወረዳ አነቢ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር የሻንበል እውነቱ እና በጎዛምን ወረዳ የአጭራ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ነጠሩ አዘነ፤ በዘርፉ ልማት ተጠቃሚ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
በአረንጓዴ ልማት የተራቆቱ አካባቢዎች በመልማታቸው እንዲሁም ዘመናዊ የንብ ማነብ አሰራር ተግባራዊ ማድረጋቸው በዘርፉ ልማት ስኬታማ ስለመሆናቸው አንስተዋል።
በመሆኑም ሌሎች አርሶ አደሮችም ከግብርና ስራቸው በተጓዳኝ በንብ ማነብ ስራ ቢሰማሩ አትራፊ እና ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ምክራቸውን ለግሰዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን አሁን ላይ ከ160 ሺህ በላይ የንብ ቀፎዎች በምርት ስራ ላይ መሆናቸውን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025