🔇Unmute
ጅግጅጋ፤ ህዳር 11/2018 (ኢዜአ)፦ በሌማት ትሩፋት ውስን ቦታን በማልማት የአመጋገብ ሥርዓታቸውን ከማሻሻል ባለፈ የሥራ ባህላቸውን እየለወጡ መሆናቸውን በጅግጅጋ ከተማ የመርሃግብሩ ተሳታፊዎች ተናገሩ።
የሌማት ትሩፋት መርሃግብር በውስን ቦታ ላይ አትክልትና ፍራፍሬን እንዲሁም እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦን በዘመነ መንገድ በማልማት ማዕዱን ምሉዕ ከማድረግ ባለፈ የአመጋገብ ስርዓቱን ለማሻሻል እንዲያስችል ታስቦ የተተገበረ ነው።
በዚህ መርሃ ግብርም በከተማም ሆነ በገጠሩ የአገሪቷ ክፍሎች በዘርፉ የተሰማሩ ሰዎች አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በእንስሳትን ተዋጽኦ ስራ ላይ በመሰማራት ከራሳቸው አልፈው ለገበያ ማረጋጋት የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸው ታውቋል።
የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎችም በእንስሳት፣ በአትክልትና ፍሬፍሬ እንዲሁም በሌሎች የከተማ ግብርና ዘርፎች ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛሉ።
በከተማው በዘርፉ ከተሰማሩ ነዋሪዎች መካከል አቶ ከድር ዓሊ አንዱ ሲሆኑ በሌማት ትሩፋት መርሃግብር ባላቸው አነስተኛ መሬት ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
በጓሮአቸው ያላቸውን ውስን ቦታን በአግባቡ ተጠቅመው የተለያዩ የአትክልት አይነቶች በማምረት ከራሳቸው አልፎ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ወይዘሮ ፋጡማ አደን በበኩላቸው በሌማት ትሩፋት መርሃግብር የጓሮ አትክልት በማምረት ቤተሰባቸውን በተሟላ ማዕድ ከመመገብ አልፈው ለገበያ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።
በተለይም ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ቃሪያና ሌሎችንም በማምረት ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸው፤ ሌሎችም ውስን ቦታ ያላቸው ሰዎች የእሳቸውን አርአያ ተከትለው አልምተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ መክረዋል።
ከዕለት ሥራቸው ጎን ለጎን በሌማት ትሩፋት መርሃግብር የጓሮ አትክልት በማልማት ገቢያቸውን እያሳደጉ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ አቶ አብዲ ቼህ ናቸው።
አቶ አብዲ እንደሚሉት በአቅራቢያ ያሉትን የውሃ አማራጮችን በአግባቡ በመጠቀም ባላቸው ጓሮ ላይ ውጤታማ ስራ መስራት ችለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025