የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በአፋር ክልል የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የመስኖ ልማት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል

Jul 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሰመራ፤ ሰኔ 23/2018(ኢዜአ)፡- የአርብቶ አደሩን ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የመስኖ ልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የአፋር ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ገለፀ።

የአፋር ክልል ከአየር ንብረት መለዋወጥና ከድርቅ ስጋት ለመውጣት በዋናነት በዝናብ ጥገኝነት ላይ የነበረውን የአርብቶ አደር ሕይወት ወደ መስኖ ልማት ለማሸጋገር ባለፉት ዓመታት ሰፊ መሠረት ጥሏል።

በተለይም የወንዝ ተፋሰስንና የከርሰ ምድር ውሃን ጥቅም ላይ ለማዋል የተጀመሩ ሰፋፊና አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች የአርብቶ አደሩን ማኅበረሰብ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የእንስሳት መኖ እጥረትን ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮም ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት የተገነቡ የመስኖ መሠረተ ልማቶች ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት እንዲበቁና አዳዲስ ፕሮጀክቶችም በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

ቢሮው ከአፋር አርብቶ አደር ልማት ማህበር ጋር በመተባበር በገቢረሱ ዞን ሃሩካ ወረዳ በፀሐይ ብርሃን የሚሰራ የመሰኖ ስራን ዛሬ ወደስራ ማስገባቱም የዚሁ ጥረት አካል ነው።


የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢንጂነር ወልአ ዊቲካ በወቅቱ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አርብቶአደሩ የመስኖ ስራዎችን በማጠናከር ተጠቃሚ እየሆነ ነው ብለዋል።

ዛሬ በወረዳው ወደ ስራ የገባው በፀሐይ ብርሃን የሚሰራ የመሰኖ ፕሮጀክቱ የመስኖ ስራን ሊያጠናክር የሚችልና ከ230 ሄክታር በላይ መሬት ማልማት የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በጎርፍ መከላከል ላይ በተሠሩ ጠንካራ ሥራዎች የለመደውን መሬት ወደ ልማት ለማስገባት ይህ በፀሐይ ብርሃን የሚሠራው የመስኖ አማራጭ ወሳኝ መሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል።

አርብቶ አደሩ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ በመጠቀም፣ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት ተጠቃሚነቱን ማሳደግ እንደሚችልም ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአዋሽ ተፋሰስ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደን አብዶ በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል የተከናወኑ የጎርፍ መከላከል ሥራዎች አካባቢዎቹን ከሥጋት ነፃ በማድረግ ወደ ልማት እንዲገቡ ማስቻላቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ሶስት ሺህ አባወራዎችን ከጎርፍ ሥጋት ነፃ ማድረግ መቻሉን የገለጹት ኃላፊው፤ በአሁኑ ወቅት 500 አባወራዎች በፀሐይ ብርሃን የመስኖ ልማት ተጠቃሚ መሆን የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026