🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ውጤታማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር እንደሚያስችል የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት ትግበራ መርሃ-ግብር እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፤ ለሀገራት ልዕልና መለኪያው የማምረቻው ዘርፍ የደረሰበት ደረጃ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም በኢትዮጵያ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራቱ ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።
በተለይም በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ በማምረቻው ዘርፍ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ዘርፉ ለሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ያለው ድርሻ ማደጉን፣ ገቢ ምርቶችን የመተካት ሂደት መሻሻሉን እና የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ማደጉን ጠቅሰዋል።

አሁን ይፋ የተደረገው የብሔራዊ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሀብት ልየታ ጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ በየአካባቢው የሚገኙ እምቅ ሀብቶችን፣ መሠረተ ልማቶችን እና ሌሎች ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን የተሟላ መረጃ የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።
ይህ የተሟላ መረጃ ደግሞ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
ጥናቱ ወደፊት ለሚከናወኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ትክክለኛውን አቅጣጫ የሚያመላክት ከመሆኑም በላይ፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በስፋት ለመሳብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጨምረው ገልጸዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026