🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ በግብርናው ዘርፍ የ7 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት ይመዘገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው፣ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት የሥራ አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው እንዳመለከቱት፤ በበጀት ዓመቱ በግብርናው ዘርፍ የ7 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት ይመዘገባል።
መንግሥት የጀመራቸው አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በተከታታይ የዕድገት ጎዳና ላይ እንዲገኝ አስችለውታል ነው ያሉት።
በዚህም መሠረት በግብርናው ዘርፍ በሁሉም አመላካቾች 7 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል ሲሉም ተናግረዋል።
ለዚህ ዕድገት መመዝገብ የመስኖ ልማት፣ የግብዓት አቅርቦት መሻሻል፣ የዘመናዊ ማሽነሪዎች አጠቃቀም ማደግ እና የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ በስፋት መተግበሩ በምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም ዘንድሮ 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በተለያዩ ስትራቴጂካዊ የልማት ውጥኖች የተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ በተሠሩ ጠንካራ ሥራዎች ኢትዮጵያ በአቮካዶ ምርት ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ ላኪ ሀገር መሆን መቻሏን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ቀደም ሲል በድርቅ ተደጋጋሚ ፈተና ይደርስበት የነበረው የቦረና አካባቢ፣ በአሁኑ ወቅት ስንዴ በማምረት ረገድ ከፍተኛና አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን በማሳያነት አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ከቡና ወጪ ንግድ ከዚህ ቀደም ባለፉት 17 ዓመታት ውስጥ በድምሩ ያገኘችው 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ብቻ እንደነበር የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዘንድሮ ግን በአንድ በጀት ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ተናግረዋል።
ይህ ትልቅ ስኬትና ዕድገት ሊመዘገብ የቻለውም የቡና ምርታማነትን በማሳደግ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመሠራቱ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026