🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ያስቻለ አቅም መገንባቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመገኘት፣ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥትን አፈጻጸም በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ የ2018 በጀት ዓመት ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ ለዜጎች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በስፋት የሥራ ዕድል የተፈጠረበት ስኬታማ ዓመት መሆኑን አስታውቀዋል።
መንግሥት የሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ ባከናወናቸው ዘርፈ-ብዙ ተግባራት በአጠቃላይ ከ5 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል አቅም መገንባቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህ በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰው በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከ600 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የዲጂታል ዕድሎችን በመጠቀም ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ ዜጎችን በርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለዜጎቿ አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት፣ በብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የሰራቻቸው አበረታችና ስልታዊ ሥራዎች ውጤት መሆኑን አብራርተዋል።
ነገ ከዚህ የተሻለ ከፍተኛ የስኬት ደረጃ ላይ ለመድረስ ግን ዜጎች ለሥራ ያላቸውን ባህል መቀየርና መትጋት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
በተለይም ወጣቶች ወጣ ብለው የመሥራትና የመንቀሳቀስ ልምዳቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባም መክረዋል፡፡
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026