የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በክልሉ በዘመናዊ ግብርና የእንስሳት ሀብት ምርታማነትን የማሳደግ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል 

Jul 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ ፤ ሐምሌ 1/ 2018 (ኢዜአ):- በአማራ ክልል በዘመናዊ ግብርና የእንስሳት ሀብት ምርታማነትን በማሳደግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ "ዘመናዊ ግብርና ለሁለንተናዊ ልዕልና" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በደሴ ከተማ ተካሒዷል።


በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) እንደገለጹት፤የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ለወጭ ንግድና ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚተርፍ ምርት ለማምረት ርብርብ እየተደረገ ነው።

በዚህም በዘመናዊ አሰራር፣ የምርት ማሳደጊያ ግብአት በመጠቀም፣ በሜካናይዜሽንና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይ በክልሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ በዘመናዊ ግብርናና እንስሳት ሀብት ልማት የተጀመረው ስራ ምርታማነትን በማሳደግ ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰረት እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም በምርምር የታገዙ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።

አርሶ አደሩ የሚያገኘውን እርጥበት ተጠቅሞ ፈጥኖ የዘር ስራውን እንዲጀምር፣ ውሃ እንዲያሰባስብ ፣ ፈጥነው የሚደርሱና ድርቅን የሚቋቋሙ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን እንዲጠቀም ማድረግ እንደሚያስፈልግ ነው ያመላከቱት ።

ለዚህም መንግስት ምርታማነትን ለማሳደግ ቴክኖሎጂና ግብዓቶችን በስፋት እያቀረበ እንደሚገኝም ገልጸዋል።


የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፤የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል በጥራት እንዲመረት ከማድረግ አኳያ አበረታች የሆኑ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በተለይም በሌማት ትሩፋት የወተት፣ የስጋ ፣ የእንቁላል ፣ የማር ፣ የዓሳና የሌሎችንም ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ዜጎች ጥሪት እንዲያፈሩ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ሲሉ ገልጸዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ደመቀ አድማሱ በበኩላቸው፣ በዞኑ በምርምር የወጡ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።


በተለይ ድርቅን የሚቋቋሙ፣ ምርታማና ፈጥነው የሚደርሱ ምርጥ ዘሮችን ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እንዲቻልም ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተገኝ አባተ በበኩላቸው፣ በተሻሻለ አሰራርና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026