የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓት በመተግበር አልሚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ ተችሏል

Aug 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጋምቤላ፤ነሐሴ 3/2018 (ኢዜአ)፦ሀገሪቱ ያሏትን የኢንቨስትመንት እድሎች ለባለሀብቶች የማስተዋወቅ እና አገልግሎቶችን ቀልጣፋ የሚያደርጉ አሰራሮችን በመተግበር በርካታ አልሚዎችን ወደ ሀገር ውስጥ መሳብ መቻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።

የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የኢንቨስትመንት አስፈፃሚ አካላት በጋምቤላ ከተማ እያካሄዱት ባለው የጋራ ምክክር በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በአዲሱ በጀት ዓመት እቅድ በመምከር የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


‎በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ አልሚዎችን ለመሳብ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያስገኙ ነው።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ብቻ 528 የውጪ ሀገር ባለሃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

''ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026 ፎረም’’ የኢንቨስትመንት ስምምነትንም የፈረሙ ሰባት ተቋማት 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ፈሰስ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ‎የዲጂታል አገልግሎቱን በማስፋትና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከርና የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ተመራጭነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የኮሚሽኑ የስፔሻል ኢኮኖሚ ዞን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ዝናቡ ይርጋ በበኩላቸው፥ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ወደ ውጤት በመቀየር የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራሩ ይጠናከራል ብለዋል።


ለዚህም የመሰረተ ልማት አውታሮችን ተደራሽነት የማስፋትና የአሰራር ማእቀፎችን ማስፋት ላይ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የሚተገበር መሆኑን ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፥ ባለሃብቶች ለሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ቅንጅታዊ አሰራሮችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

የምክክር መድረኩ በ2018 እቅድ አፈፃፀምና በአዲሱ በጀት ዓመት ውይይት በማድረግ የትኩረት አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ተሳፊዎች በዛሬው ዕለት ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ጋር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።


በቀጣይም የልማት ምልከታ የመስክ ጉብኝት በማካሄድ መርሃ ግብራቸውን እንደሚያጠናቅቁ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...

Jul 13, 2026

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ምህዳር ፈጥሯል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...

Jul 9, 2026