የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ምህዳር ፈጥሯል

Jul 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ምህዳር መፍጠራቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ።

በኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ለንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፉ የተመቻቸ ምህዳር መፍጠር ይገኝበታል።

ይህንን ተከተሎም መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰዱ በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ፍሰት እየጨመረ ነው።

ኢዜአ ኢትዮጵያ ለውጭ ቀጥታ የኢንቨስትመንት የፈጠረችውን ምቹ ሁኔታ በተመለከተ የተለያዩ ሀገራትን አምባሳደሮችና ተወካዮችን አነጋግሯል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር)፥ እስራኤልና ኢትዮጵያ የጠበቀ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል።

እስራኤል በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንትና የንግድ ዘርፎች ላይ በመሰማራት ለጋራ እድገት አበክራ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።

እስራኤል ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎች ምርቶች እንደምታስገባ ጠቅሰው፥ እስራኤልም ያላትን የቴክኖሎጂ አቅምና እውቀት ለኢትዮጵያ በማካፈል ላይ እንደምትገኝ አክለዋል።

ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ማድረጓ እና ሀገሪቱ ወደ ዲጂታላይዜሽን የምታደርገው ፈጣን ግስጋሴ፣ በአሁኑ ሰዓት ለኢንቨስትመንት ምቹ ምህዳር ያላት ሀገር እንዳደረጋት ገልጸዋል፡፡

ይህም እስራኤል በኢትዮጵያ ያላትን ኢንቨስትመንት ይበልጥ እንድታስፋፋ ምቹ መደላድል እየፈጠረ መሆኑን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡


በኢትዮጵያ የስሪላንካ አምባሳደር ኒርማላ ፓራናቪታና በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ መድረኮች ለንግድና ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ምቹ ሁኔታዎች ለማስተዋወቅ የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

እንዲሁም የምታቀርባቸው የተለያዩ ማበረታቻዎች ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ አስታውቀዋል፡፡

ስሪላንካ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ላይ በስፋት ኢንቨስት እያደረገች እንደምትገኝ አንስተው፣ በቀጣይም በሌሎች አማራጭ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ለመሰማራት ትልቅ ፍላጎትና ቁርጠኝነት እንዳላት ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፓኪስታን የንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ተወካይ ባሲት ሳሊም ሻህ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለንግድ ግንኙነትና ለኢንቨስትመንት እጅግ ምቹ የሆነ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።


ፓኪስታን በአሁኑ ወቅት የተወሰኑ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ምርቶችን ወደ ሀገሯ እያስገባች መሆኑን የገለጹት ተወካዩ፤ ከእነዚህም መካከል ቡና እና ጥራጥሬ ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፓኪስታን ወደ ሀገሯ ልታስገባቸው የምትፈልጋቸው ዘርፈ-ብዙ ሀብቶች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ በቀጣይም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ውብ የቱሪዝም ጸጋዎችን የተቸረች ሀገር መሆኗን ገልጸው፥ ፓኪስታን ኢትዮጵያ ጋር በቱሪዝምና ሌሎች ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026