የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ወጣት አዝመራው ታደሰ በኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የስኬት ምዕራፍ

Aug 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወጣት አዝመራው ታደሰ የ 5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ተመራቂ ወጣት ባለሙያ ነው።

ወጣቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈትቤት በ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ዙሪያ ባዘጋጀው የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ተሞክሮውን አካፍሏል፡፡

ወጣት አዝመራው በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳለው ፥ ይህንን ታላቅ ዕድል በዩኒቨርሲቲ ቆይታው የመጨረሻ ዓመታት ውስጥ በመቀላቀል አስደናቂ የስኬት ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ወጣቱ ኮድ ማድረግን መማር ከጀመረበት ጥረት ተነስቶ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ኮደሮችን የሚያገናኝ ድረ ገጽ ወደ ማበልጸግ መሸጋገር መቻሉንና ዛሬ ደግሞ ፉል ስታክ ድረ ገጽ አልሚ መሆኑን አስረድቷል።

በሰርተፍኬት ብቻ አትወሰኑ የሚለው ወጣት አዝመራው የተማራችሁትን በተግባር በማዋል እና በመለማመድ እውነተኛ ዕድገት ማምጣት ትችላላችሁ ሲል ተናግሯል።

‎በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም እንዳሉት ፥ የወጣቶች የቴክኒክና የዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት ነው፡፡

በዚህ ክረምት የኮደሮችን ቁጥር 7 ሚሊየን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026

የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃት የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...

Jul 13, 2026

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ምቹ ምህዳር ፈጥሯል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...

Jul 9, 2026