🔇Unmute
ጅማ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን በዘንድሮው የምርት ዘመን የኦቾሎኒ ልማትን በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጅማ ዞን በተለምዶ በቡና፣ በበቆሎና በቅመማ ቅመም አምራችነቱ የሚታወቅ ቢሆንም፣ በቅርብ ዓመታት የሰብል ስብጥርን ለማስፋትና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ የቅባት እህሎች ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል።
በዞኑ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በሚደረገው ጥረት የአትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የኦቾሎኒ ልማት ዋናው ትኩረት ሆኗል።
በዚህም በዞኑ በዘንድሮው የምርት ዘመን 40 ሺህ 512 ሄክታር መሬት ላይ ኦቾሎኒን በማልማት ከ920 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ነው።

የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም ለኢዜአ እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት ለግብርናው በተሰጠው ትኩረት ከተለምዷዊ ሰብሎች በተጨማሪ እንደ ኦቾሎኒ እና ሱፍ ያሉ የቅባት ዕህሎች ልማት እየተስፋፋ መጥቷል።
በተለያዩ የዞኑ ወረዳዎች የኦቾሎኒ ልማትን በማስፋፋት ከፍተኛ ምርት ለማግኘት በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በዘንድሮው የምርት ዘመንም ልማቱ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።
ከኦቾሎኒ በተጨማሪ ሱፍም በ3ሺህ 300 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ መሆኑን ጠቅሰው፣ የቅባት ዕህሎቹን ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፎች እና የክትትል ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ የቅባት ዕህሎችን ልማት በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚከናወነው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በዞኑ ጮራ ቦቶር ወረዳ ኦቾሎኒን እያለሙ ያሉት አርሶ አደሮች አህመድ ሼህ መሀሙድ እና አራርሴ ቦሩ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት ከኦቾሎኒ ልማት ጥሩ ውጤት ማግኘታቸውን ገልጸው፣ በዘንድሮው የምርት ዘመን የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአየር ማረፊያው ለአገልግሎት መብቃትም የአካባቢውን የንግድ፣የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማ...
Jul 13, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና የዲጂታል አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠና...
Jul 9, 2026