🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
“ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል።
ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል።
ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል።
በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል።
ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው።
በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው።
ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል።
ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል።
የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል።
እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል።
ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው።
በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል።
ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል።
በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።
የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026