🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ስኬት ቀጣናዊ ትስስርን በማፋጠን የጋራ ብልፅግናን የሚያበስር አህጉራዊ የልማት አጀንዳ መሆኑ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በስኬት የቋጩበት መንገድ ለአፍሪካዊያን የልማት ፍላጎት ትልቅ ትምህርት የሚያስተላልፍ አህጉራዊ የልማት አጀንዳ መሆኑንም ገልጸዋል።
የደቡብ ሱዳን የውሃና መስኖ ሚኒስትር ጀምስ ማዊች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በውሃ ሃብት ልማትና አስተዳደር የምትወስደው ቁርጠኛ አመራር የሚደነቅ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የውሃና የኃይል አቅርቦት ልማትም ቀጣናዊ የጋራ ተጠቃሚነት መርህን የተከተለና በአርዓያነት የሚወሰድ ወሳኝ የልማት እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የውሃና ኃይል አቅርቦት ልማት በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በቀጣይም የውሃ ሃብት ልማት ትብብርን በማጠናከር ቀጣናዊ የጋራ ዕድገትን ማፋጠን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የዑጋንዳ የውሃና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ቤአትሪስ አቲማንዋ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአስደናቂ የልማትና ዕድገት ጎዳና ላይ ናት ብለዋል።
በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በስኬት የቋጩበት መንገድ ለአፍሪካዊያን የልማት ፍላጎት ትልቅ ትምህርት የሚያስተላልፍ አህጉራዊ አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ልማትም ቀጣናዊ የትስስር አቅምን በማጎልበት በትብብር ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ዕድገትን እያፋጠነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችም የአፈር ለምነትና የውሃ ደኅንነትን በማስጠበቅ ለዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ጉልህ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑንም አንስተዋል።
በቀጣይም የኢትዮ-ዑጋንዳን ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር የኢትዮጵያን የልማት ስኬት ተሞክሮዎች ለማጋራት እንደሚሰሩ ጠቅሰዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026