🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦አዲሱ የመንግስት የመሠረተ ልማት ግንባታና የቤቶች ልማት እሳቤ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተሞቿን ለነዋሪዎች ምቹ፣ለኢንቨስትመንት ሳቢ እና ለቱሪዝም ተመራጭ ለማድረግ አዳዲስ የልማት ስልቶችን ስትከተል ቆይታለች።
ይህ ሀገራዊ ለውጥ በከተማ ልማት ዘርፍ መሰረታዊ ሽግግር ያመጣ ሲሆን፣ከተሞችን ከነባር መዋቅራቸው በማላቀቅ ወደ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የኢኮኖሚ ማዕከላት የመለወጥ ስራ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማ ልማት፣በውበት እና በአረንጓዴ ልማት ረገድ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ሰፊ የእግረኛ መንገዶች፣የብስክሌት መስመር እና ማራኪ እይታ እንዲኖር የተከናወነበት ሲሆን፣ይህም ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ውብ እንዲሆኑ ከማድረጉም ባለፈ የትራፊክ ፍሰቱንና የከተማ ገጽታውን በእጅጉ ቀይሮታል።
የሀገራዊ ለውጡ አንዱ ግብ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር በዘላቂነት መፍታት ሲሆን፤ የዚሁ የለውጥ ጉዞ ውጤትና የጉባ ብስራት የሆነውን የአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ቤቶች በላይ ግንባታ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ እውን ለማድረግ ታላቅ ዕቅድ ተይዞ ወደ ተግባር ተገብቷል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንደገለጹት፤ የከተማ አካባቢዎች ውድ እና በርካታ መሰረተ ልማት የሚፈስባቸው ናቸው።
ቀደም ብሎ እነዚህ ቦታዎች ከደረጃ በታች ተገንብተው ጥቅም ላይ ውለው እንደነበር አስታውሰዋል።
በአሁኑ ወቅት እነዚህ አካባቢዎች ለንግድ፣ ለመኖሪያና እና የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ዘመናዊ ግንባታዎች እየተከናወኑባቸው መሆኑን ገልጸዋል።
እነዚህ ግንባታዎች ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እየተገነቡ ከተሞችንም እየለወጡ እንደሚገኙ ጠቁመው፤አዲሱ የመንግስት የከተማ እና መሰረተ ልማት እሳቤ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አመልክተዋል።
የመደመር መንግስት የብልፅግና ጉዞ ሊሳካ የሚችለው በሚከናወኑ የዕለት ተዕለት ስራዎች መሆኑን በግልጽ ማስቀመጡን ጠቁመዋል።
የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሳለጥ ከመንግስት ጥረት በተጨማሪ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል።
በጋራ በመተባበር፣አዳዲስ ፈጠራዎችን እና ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል ይህንን ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ገልጸዋል።
ከጉባ ብስራቶች አንዱ የሆነው የአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ቤቶች ግንባታ በአምስት ዓመት ውስጥ እውን ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል።
ይህንን ለማሳካት የመንግስት የሆነው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና የግል ዘርፉን በማሳተፍ ጥረቶች እንደሚደረጉ ተናግረዋል።
የቤት አቅርቦት ፍላጎትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026