🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል በግብርናው ዘርፍ በተከናወኑ ስራዎች የቤተሰብ ብልፅግና ማረጋገጥ ያስቻሉ ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ ገለፁ።
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ እና የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

እንዲሁም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሸን ኮሚሽነር ወገኔ ብዙነህ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለማ መሰለ(ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና የግብርና ሙያተኞች ተገኝተዋል።
የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ በክልሉ ልዩ ፀጋዎችና ዕድሎችን በመለየት የተለያዩ ኢኒሼቲቮች ተቀርፀው ወደ ትግበራ መገባቱን ገልጸዋል።
በዚህም በሰብል፤ በአትክልትና ፍራፍሬና በቅመማቅመም እንዲሁም በእንስሳት ሀብት ልማት የክልሉን አቅም እና የገበያ ዕድሎችን በመለየት በተከናወኑ ስራዎች የቤተሰብ ብልፅግና ማረጋገጥ ያስቻሉ ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን ገልፀዋል።
በቀጣይም ስኬቶችን በማስቀጠል ተረጂነትን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት በየደረጃው የመግባባትና ማቀናጀት ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሸን ኮሚሽነር ወገኔ ብዙነህ በበኩላቸው በክልሉ በአብዛኛው ዞኖች የሴፍትኔት ተጠቃሚ እንደነበሩ አንስተዋል።
በዚህም እንደ ሀገር የተያዙ ራስን የመቻል ግቦችን በመከተል በክልሉ ያሉ ፀጋና ዕድሎችን ለይቶ ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራቱን ጠቅሰዋል።
በዚህም ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል።
ለአብነትም ከጥቂት ዓመት በፊት እህል ሲሰፈርላቸው የነበሩ በርካታ አርሶ አደሮች አሁን ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት እያንቀሳቀሱ መሆኑን አንስተዋል።
ክልሉ ተረጂ የነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎቹን ከሌማት ትሩፋት፣ ከአረንጓዴ አሻራና ከሌሎች ሀገራዊ ኢኒሼቲቨች ጋር በማስተሳሰር ምርታማ የሆኑ አርሶ አደሮች መፍጠር መቻሉን ነው የገለፁት።
በተመሳሳይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለማ መሰለ(ዶ/ር) ከልመና ወደ ብልፅግና የመሻገርና ሀገራዊ ክብርን የማስጠበቅ ግብ በመሰነቅ ወደ ትግበራ መገባቱን አንስተዋል።
ለዚህ ደግም የክልሉን ልዩ ፀጋና አቅም በመለየት በተሰሩ ስራዎች ከክልል አልፈው ለሀገር የተረፉ የግብርና ምርቶች እየተመረቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም በተረጂነት ሕይወት ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ምርታማ የማድረግ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ገልጸዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026