የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ የአካባቢውን ኢንቨስትመንት ያሳድጋል

May 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ማርቆስ ፤ ግንቦት 13/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጠናቀቅ የአካባቢውን የኢንቨስትመንት፣ የንግድና ቱሪዝም ልማት በማፋጠን የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ነው ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ገለጹ።

የከተማ አስዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ አቶ ተመስገን ተድላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአውሮፕላን ማረፊያው የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠን የላቀ ድርሻ አለው።


በተለይ ባለሃብቶች ያጋጥማቸው የነበረውን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ ፕሮጀክቶቻቸውን በቅርበት ለመከታተልና ፣ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚመረቱ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ከማቅረብ በተጨማሪም የአውሮፕላን ማረፊያው አዳዲስ ባለሃብቶችን ለመሳብም መልካም እድል ይዞ መምጣቱን አስረድተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አእምሮ በበኩላቸው፤ የአውሮፕላን ማረፊያው የቱሪዝም ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ መሆኑን ገልጸዋል።


በዋናነትም የአባይ በረሃን አቋርጦ በመምጣት በአካባቢው የሚገኙ ቅርሶችን ለመጎብኘት ያጋጥም የነበረውን ችግር በመቅረፍ የጎብኝዎችን ቁጥር ለመጨመር የሚያስችል ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም የጮቄ ተራራን፣ ጥንታዊ ገዳማትና ሌሎች ቅርሶችን ለጎብኝዎች ክፍት ለማድረግም አሰጎብኝዎችን ከማደራጀት ጀምሮ ምቹ መስተንግዶ ለማቅረብ በተለየ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ኢንጅነር ሙሉጌታ ይስማው በበኩላቸው፤ የአውሮፕላን ማረፊያው መገንባት የዘመናት የህዝብ ጥያቄን በመፍታት የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳደግ የሚያስችል ነው ብለዋል።


አካባቢው በግብርናው ዘርፍ ትርፍ አምራች ከመሆኑም በላይ ያለውን የማዕድን ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም ከተማዋን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማእከል ለማድረግ መልካም እድል ይዞ መምጣቱን ጠቁመው ይህም በአገልግሎት ዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል ።

በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በግንባታ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎችን ፈጥኖ በማጠናቀቅ አካባቢውን የንግድ ማእከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ተደርጓል

ድሬደዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን የድሬደዋ አስተዳ...

Jul 20, 2026

በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት እየጣለ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት መጣል መቻሉን የፌ...

Jul 7, 2026

በተያዘው ዓመት በኢንዱስትሪው የተኪ ምርቶች አቅርቦትን በማሳደግ 5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ):-በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተያዘው ዓመት የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግና የውጭ ምርቶችን በመተካት አምስት ቢሊዮን ዶላር ...

Jul 3, 2026

ቡናን በበጋ መስኖ በማልማት የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል

አዳማ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ቡናን ከመደበኛ ወቅት በተጨማሪ በበጋ መስኖ በማልማት የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት መደ...

Jun 17, 2026