🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የሥራ ገበያ ምኅዳሩን በውጤታማ የዲጂታል ሥርዓት በማዘመን ሥራና ሰራተኛ በቀላሉ የሚገናኝበት ዕድል እየተፈጠረ መሆኑን የሥራ ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል ገለጹ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር ያለማውን ሥራና ሰራተኛ በቀላሉ የሚገናኝበት 'ፈልጉልኝ' የተሰኘ ዘመናዊ የዲጂታል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል በዚሁ ወቅት፤ የዜጎችን የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያዘምኑ የዲጂታል አማራጭ የማሻሻያ እርምጃዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው ብለዋል።
ይፋ የተደረገው 'ፈልጉልኝ' የሥራና ሰራተኛ አገናኝ መተግበሪያም ሥራና ሰራተኛን በቀላሉ የሚያገናኝ የዲጂታል አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል።
ሥራና ሰራተኛ በዲጂታል ሥርዓት የሚገናኝበት መተግበሪያም በሁሉም ዘርፍ ሙያና ክህሎት ያላቸው ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት የሚያሰፋ እንደሆነ ተናግረዋል።
መተግበሪያውን ከፋይዳና የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሰርዓት ጋር በማስተሳሰር በተለያዩ የቋንቋ አማራጮች ተደራሸ የማድረግ ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል።
በመተግበሪያው የተካተቱ የተሟላና አስተማማኝ የቴክኖሎጂ አማራጮች ፍትሐዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ምኅዳርን በመፍጠር የማይተካ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
የሥራ ገበያ ምኅዳሩን በውጤታማ የዲጂታል ሥርዓት በማዘመን ሥራና ሰራተኛ በቀላሉ የሚገናኝበት ዕድል እየተፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ፤ መተግበሪያው በሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ዕውቀት የለማና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ብለዋል።
ይህም የመረጃ ሉዓላዊነትና ደህንነትን ለማስጠበቅ ተደማሪ አቅም እንዳለው ገልጸዋል።
አምስት የሀገር ዉሰጥ ቋንቋዎችና አጭር የስልክ መልዕክት አማራጭ በመተግበሪያው መካተታቸውም የዜጎች ተጠቃሚነትን ለማላቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026