የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የከተማውን አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ለንግድና ኢንቨስትመንት የበለጠ ምቹ ለማድረግ ትከረት ተሰጥቷል

May 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 18/2018 (ኢዜአ)፡- በወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግስት አገልግሎትን በማዘመን ከተማውን ለንግድና ኢንቨስትመንት የበለጠ ምቹ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱ ተገለጸ ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ለሚያስገነባው የባለ 12 ወለል የቢሮ ሕንፃ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በወቅቱ እንደገለጹት የወላይታ ሶዶ ከተማ ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ እየሆነች መምጣቷን ተከትሎ አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን አስፈልጓል።

ግንባታው የተጀመረው የከተማ አስተዳደሩ የቢሮ ህንጻ ምቹ የሆነ የስራ አካባቢ በመፍጠር የመንግስት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል ።

የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ከተማዋን ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ በሚደረገው ሂደት በቅንጅትና በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።


የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማርያም በከተማ አስተዳደሩ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የሚገነባው ዘመናዊ የቢሮ ህንፃ የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመው ህንጻው ከተማዋን ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭና ተወዳዳሪ ለማድረግ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፤

የቢሮ ህንጻው በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚገነባ መሆኑን ጠቁመው ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አስታውቀዋል ።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026