🔇Unmute
ባህርዳር ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዘንድሮው መኸር እርሻ ከ876ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ለኢንዱስትሪና ለውጭ ገበያ የሚውል የሰሊጥና የአኩሪ አተር እንደሚለማ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
ሰሊጥ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ የግብርና ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ነው።
አኩሪ አተርም ለምግብ ዘይት ፋብሪካዎችና ለእንስሳት መኖ ኢንዱስትሪዎች ወሳኝ ግብዓት ከመሆኑም በላይ፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያለው ተፈላጊነት እየጨመረ የመጣ ሰብል ነው።
በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለፁት ለኢንዱስትሪና ለወጪ ምርት ግብዓት የሚውሉ ሰብሎችን በጥራትና በብዛት ለማምረት ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው።

በዚህም በዘንድሮው የመኸር እርሻ የአየር ንበረታቸውና ስነ ምህዳራቸው ተስማሚ በሆኑ አካባቢዎች የሰሊጥና አኩሪ አተር ሰብሎች በስፋት ለማልማት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።
በዚህም በክልሉ ከሚለማው 876ሺህ 870 ሄክታር መሬት፤ 463ሺህ 566 ሄክታር በሰሊጥ ቀሪው ደግሞ በአኩሪ አተር እንደሚለማ ተናግረዋል።
ከልማቱ ከ15 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ጠቁመው የዘር ወቅት በመድረሱም ዘርና ማዳበሪያ እየቀረበ ነው ብለዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026