🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል በበልግ እና መኸር እርሻ በድምሩ 11 ሺህ 956 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ኡመር እንደገለፁት በክልሉ ያለውን አነስተኛ መሬት በአግባቡ ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
በክልሉ በ2018/19 በበልግ እና መኸር እርሻ በድምሩ 11 ሺህ 956 ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል ዓይነቶች ለማልማት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በበልግ ዝናብ እስካሁን 8 ሺህ 681 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ጠቁመው፥ ቀሪው 3 ሺህ 275 ሄክታር በክረምት መኽር ዝናብ ቶሎ ደራሽ ማሽላ እና ስንዴ ለመዝራት አሰፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ሶስት የገጠር ወረዳዎች በሚገኙ ማሳዎች ላይ እየለሙ የሚገኙት ሰብሎችም ማሽላ፣ በቆሎ እና ስንዴ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ለመኸር እርሻው ምርትና ምርታማነት ማደግ አስፈላጊው የማዳበሪያ፣ የዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓት አቅርቦት ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ያመለከቱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ በምርት ዘመኑ እየለሙ ካሉ ሰብሎች 300 ሺህ ኩንታል ምርት ለመሰበሰብ መታቀዱንም አስረድተዋል።
በየደረጃው ያሉ የግብርና ባለሙያዎችም ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን ሙያዊ እገዛና ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም አርሶ አደሩን ከዝናብ ጠባቂነት ከማላቀቅና ተጠቃሚነትን ከማሳደግ አንፃር አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል ነው ያሉት።
በቀጣይም የተገኙ አበረታች ውጤቶችን በማስቀጠል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማጎልበትና ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የላቀ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026