🔇Unmute
ጋምቤላ፤ ግንቦት 27/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል የቡና አብቃይ ወረዳዎች የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የጋምቤላ ክልል ለግብርና ኢንቨስትመንትና ለተለያዩ ሰብሎች ልማት ምቹ የአየር ንብረትና ሰፊ ለም መሬት ካላቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች አንዱ ቢሆንም፣ የቡና ልማት ዘርፉ ግን ካለው ከፍተኛ እምቅ አቅም አንጻር በተገቢው ሳይለማ ለረጅም ዓመታት ቆይቷል።
በተለይም እንደ ጋዶ፣ የጎደሬ ወረዳን ጨምሮ አንዳንድ የምዕራብ አኙዋክ አካባቢዎች ለቡና ልማት እጅግ ተስማሚ የተፈጥሮ ስነ-ምህዳር አለው።
በእነዚህ ወረዳዎች የተራቆቱ አካባቢዎችን ከአረንጓዴ አሻራ ልማት ጋር በማቀናጀት በቡናና ጥምር የጥላ ዛፍ በመሸፈን ስነ-ምህዳርን በማሻሻልና የዘርፉን ምርታማነት በመጨመር ረገድ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድሮው ቱት ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ በማጃንግ ዞን በሚገኙ የመንጌሽና የጎደሬ ቡና አብቃይ ወረዳዎች የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ ነባር ዝርያዎችን በተሻሻሉ የቡና ዝርያዎች በመተካትና በተራቆቱ አካባቢዎች የቡና ጥምር ደን ልማትን በማስፋት ምርታማነትን የማሳደግ ስራ እንደሚከናወን ነው የገለጹት።
በዘንድሮው ክረምት ከአረንጓዴ አሻራ ልማቱ ጋር በማቀናጀት በፕሮጀክቶች፣ በባለሃብቶችና በአርሶ አደሮች ከ4 ሚሊዮን በላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞች መዘጋጀታቸውን አቶ አንድሮው ተናግረዋል።

በቢሮው የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ገዳሙ እንዳሉት የተሻሸሉ የቡና ዝርያዎችን ከቴፒና ከጅማ ግብርና ምርምር ተቋማት በማምጣት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግ ተግባር እየተከናወነ ነው።
በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራሙ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለይም በጎደሬ ወረዳ በሞዴል አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም የቡና ማሳና በሰርቶ ማሳያዎች የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን የማስፋትና የማስተዋወቅ ስራ ሲከናወን መቆየቱን ገልጸዋል።
በዘንድሮው ክረምትም ከ250 ሺህ የሚበልጡ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በኩታ ገጠም ለሚያለሙና ለሌሎች ሞዴል አርሶ አደሮች ለማሰራጨት ችግኞቹ መዘጋጀታቸውን አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል።
በማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎች ካገኙ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ዝናቤ ቢለው በሰጡት አስተያየት በተራቆቱ አካባቢዎች የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ከጥምር የደን ዛፍ ጋር አቀናጅቶ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም በተመሳሳይ መልኩ የቡና ጥምር ደን ልማቱን በማስፋትና ተጠቃሚ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ድጋፍ የተራቆቱ አካባቢዎችን በቡናና በጥምር የጥላ ዛፍ በማልማት አካባቢውን ወደ ነበረበት በመመለስና ከዘርፉም ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው የዚሁ ቀበሌ አርሶ አደር አቶ ከድር ሙሀመድ ናቸው።

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026