የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በክልሉ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ ህዝብን ከወጪና እንግልት ለመታደግ የተጀመሩ ተግባራት ይጠናከራሉ

Jun 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አርባ ምንጭ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስታዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ ህዝብን ከወጪና እንግልት ለመታደግ የተጀመሩ ተግባራት ይጠናከራሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

በአርባ ምንጭ ከተማ የተገነባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።


ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ እያስቻለ ነው።

በክልሉም በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ እና በዲላ ከተሞች ማዕከሉን ተደራሽ በማድረግ ህዝቡ ባለበት ሆኖ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።


በዲጂታል ሥርአት ታግዞ የሚሰጠው አገልግሎት ለዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ጉልህ ፋይዳ አለው ያሉት አቶ ጥላሁን፣ አገልግሎቱ ፈጣንና ከሙስና የጸዳ በመሆኑ የዜጎችን እርካታ ከፍ ያደርገዋል ብለዋል።

ማዕከሉ ዜጎች ወደክልሉ የተለያዩ ከተሞች ሳይሄዱ የፌደራል ተቋማት አገልግሎቶችን ጭምር በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በክልሉ መንግስታዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ ህዝብን ከወጪና እንግልት ለመታደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አልማዝ መሰለ በበኩላቸው ማዕከሉ ሰው ተኮር እንደሆነና በመንግስት አገልግሎት ላይ ይታዩ የነበሩ ችግሮችን በመሠረታዊነት የሚፈታ ነው ብለዋል።


የተገልጋዩን ጊዜ፣ ጉልበት እና ወጪ የሚቀንስ መሆኑን ጠቅሰው፣ ውጤታማና ለዜጎች ክብር የሰጠ አገልግሎት በመሆኑ ህዝብና መንግስትን በማቀራረብ ለሀገሪቱ ብልጽግና ጉዞ ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል።

"መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መንግስት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል" ያሉት ደግሞ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉቀን ቀሬ ናቸው።


አገልግሎቱ በዲጂታል ሥርአት የታገዘ በመሆኑ ህዝቡን በፍትሃዊነት ለማገልገል፣ መረጃን በአግባቡ ለማደራጀት እንዲሁም የተገልጋይ እንግልትን ለማስቀረት ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ413 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መገንባቱን ገልጸዋል።


በማዕከሉ የምረቃ መርሀግብር ላይ በየደረጃው ካሉ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተጨማሪ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ማዕከሉ አራት የፌደራልና አምስት የክልል ተቋማትን በአንድነት ያጣመረ ሲሆን ከ32 በላይ አገልግሎቶችም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው የሚሰጡበት መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026