የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!

Jun 14, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

በኢዜአ ዐይን ...!

በዮሐንስ ደርበው

የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ።


አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው።


አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል።


አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል።


በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል።


አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል።

በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም

ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው።


ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል።



የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል።


በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል።


አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል።


ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል።


ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው።


#በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ


#Ethiopian_News_Agency

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ተደርጓል

ድሬደዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን የድሬደዋ አስተዳ...

Jul 20, 2026

በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት እየጣለ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት መጣል መቻሉን የፌ...

Jul 7, 2026

በተያዘው ዓመት በኢንዱስትሪው የተኪ ምርቶች አቅርቦትን በማሳደግ 5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ):-በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተያዘው ዓመት የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግና የውጭ ምርቶችን በመተካት አምስት ቢሊዮን ዶላር ...

Jul 3, 2026

ቡናን በበጋ መስኖ በማልማት የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል

አዳማ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ቡናን ከመደበኛ ወቅት በተጨማሪ በበጋ መስኖ በማልማት የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት መደ...

Jun 17, 2026