የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ዘርፍ የጀመራቸውን ሥራዎች በማጠናከር፣ የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሠራል

Jun 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሰመራ፣ሰኔ 16/2018(ኢዜአ)፡- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ዘርፍ የጀመራቸውን ሥራዎች በማጠናከር፣ የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተገለጸ።

ዩኒቨርሲቲው የክልሉን የአምስት ዓመት የገቢ ጥናት ህትመት አጠናቆ በዛሬው ዕለት ለክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስረክቧል።

የአፋር ክልል ያለውን ሰፊ የኢኮኖሚና የንግድ አቅም በመጠቀም የውስጥ ገቢውን ማሳደግ እና የልማት ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም መደገፍ ከክልሉ መንግስት ዋና ዋና ትኩረቶች መካከል አንዱ ነው።

ይሁን እንጂ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ዘመናዊ ከማድረግ፣ የግብር ከፋዩን መሠረት በትክክል ከመለየት እና ሊሰበሰብ የሚችለውን እውነተኛ የገቢ አቅም በጥናት ላይ ተመስርቶ ከመተንበይ አኳያ ሰፊ ክፍተቶች ሲታዩ ቆይተዋል።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የክልሉን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማገዝ ከወሰዳቸው ቁርጠኛ እርምጃዎች መካከል አንዱ የምርምር ስራዎቹን ከክልሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፍላጎት ጋር ማጣጣም ነው።

በተለይም የክልሉን የገቢ አቅም በሳይንሳዊ መንገድ ማጥናት የመንግስትን የፖሊሲ እና የውሳኔ አሰጣጥ አቅም ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ይታመናል።

በዚህም መሰረት፣ ዩኒቨርሲቲው በምርምር ዘርፍ የጀመራቸውን ስራዎች ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ትልቅ ማሳያ የሚሆን ስራ አከናውኗል።

ተቋሙ በክልሉ ያለውን የገቢ አሰባሰብ እና የወደፊት አቅጣጫ የሚያሳይ የአምስት ዓመት የገቢ ጥናት ህትመት አጠናቆ በዛሬው ዕለት ለክልሉ ገቢዎች ቢሮ ማስረከቡም የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው።


በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አወል አብዱ እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲው ባስረከበው ጥናት መነሻነት ከወረዳ እስከ ቀበሌ የሚገኙ የክልሉን የገቢ ሀብቶች በትክክል መለየት ተችሏል።

የጥናቱ ሪፖርት ከእንስሳት ሀብት ጀምሮ ያሉትን የተፈጥሮ ጸጋዎች ለመለየትና በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በትኩረት መሥራት እንዲችሉ ትልቅ እገዛ ማድረጉንም አስረድተዋል።

የክልሉን ሀብቶች አሟጦ ለመጠቀም ለሚደረገው ጥረት ጥናቱ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት ኃላፊው፤ የተገኘው የጥናት ውጤትም በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ እንደሚውል አረጋግጠዋል።

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ዓሊ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ለምርምርና ጥናት ሥራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለማኅበረሰቡ ተጠቃሚነት በትጋት እየሠራ ይገኛል።

ይህ ጥናት የክልሉን የገቢ ምንጮች ለማስፋት፣ የታክስ አስተዳደሩን ለማዘመን እና በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚሰበሰበውን ገቢ በዕቅድ ለመምራት እንደ ታላቅ መተግበሪያ የሚያገለግል መሆኑን ገልጸው፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን የምርምርና የተግባር ትስስርንም ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ክንውን ነው ብለዋል።

አቶ አደም እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ተኮር ሥራዎችን በትብብር እያሰፋ ይገኛል።

ለዚህም ማሳያ የሚሆነው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት (ከ2016 እስከ 2020 ዓ.ም) የሚጠቀምበት የገቢ ሀብት ጥናት ተጠናቆ መቅረቡ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026