🔇Unmute
ድሬደዋ፣ ሰኔ 22/2018(ኢዜአ)፡- በዘንድሮ በጀት አመት ከ 7 ሺህ 7 መቶ በላይ የገጠር ቤተሰቦች ከተረጂነት ወደ አምራችነት መሸጋገራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።
ተረጂነትን የሚጠየፍ አምራች ማህበረሰብ የማፍራትና በዘርፉ ለተገኙ ውጤቶች እውቅና የመስጠት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተገለፀው።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሚስራ አብደላ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ ዝናብ አጠር በሆነው በድሬደዋ ገጠራማ አካባቢዎች ማህበረሰቡ ከጠባቂነትና ከተረጂነት ወጥቶ ምርታማ እንዲሆን በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል።
ባለፉት አምስት አመታትም በአነስተኛ መስኖ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በሰብልና በፍራፍሬ እንዲሁም በተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ የተከናወኑ ተግባራት ህብረተሰቡን ከገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ወደ አምራችነት አሸጋግሯል ብለዋል።
በተለይም የገጠሩን ክላስተር ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተከናወኑት ተግባራት ተረጂነት የሚጠየፍ ትውልድ በማፍራት ውጤት እንዲመዘገብበት አድርጓል ነው ያሉት።
አርብቶ አደሩ እና አርሶ አደሩ ማሕበረሰብ በተፈጥሮ ሃብቱና በተገነቡት መሰረተ ልማቶች በመታገዝ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚያደርገውን ጉዞ ለማሳለጥ እንዳስቻለም ነው የተናገሩት።
ለአብነትም ኡሉል ሞጆ የገጠር ቀበሌ ህብረተሰብ ሙሉ በሙሉ ከተረጂነት ወደ አምራችነት መሸጋገሩንም ነው ኃላፊዋ ያነሱት።
በዘንድሮው በጀት ዓመትም 7 ሺህ 7መቶ በላይ የገጠር ቤተሰብ ከተረጂነት ወደ አምራችነት መሸጋገራቸውን ገልጸዋል ።
በግብርና፣ በአነስተኛ የንግድ ስራዎች ሽግግር ላደረጉት አርሶ እና አርብቶ አደሮች ለስራቸው መቀላጠፍ የመነሻ ካፒታልና ሙያዊ ድጋፍ መደረጉንም አንስተዋል።
ከተረጂነት ለተሸጋገሩት የህብረተሰብ ክፍሎች በዚህ ወር መጨረሻ ዕውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥም ነው የገለጹት።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026