🔇Unmute
አዳማ፤ ሐምሌ 13/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በተካሄደ የኦዲት ክትትል ግኝቶች ላይ አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ መደረጉን የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ኃላፊ አቶ ተፈሪ ወንድይፍራው ተናገሩ።
ለሁለት ቀናት የተካሄደው የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉን ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርትን እና የዳኞች ሹመትን በማፅደቅ ተጠናቋል።

የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን ሪፖርት ያቀረቡት ኃላፊው አቶ ተፈሪ ወንድይፍራው፤ የመንግሥት ገቢ እና ወጪ በሕግና መመሪያ መሠረት መሰብሰቡን እና መውጣቱን ለማረጋገጥ ኦዲት መደረጉን ተናግረዋል።
በኦዲት ሥራውም በ48 መሥሪያ ቤቶች 195 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ሳይሰበሰብ መገኘቱን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ከ220 ሚሊዮን ብር በላይ ሕግን ሳይጠብቅ የበጀት ዝውውር ሥራ ላይ መዋሉ በተደረገው ኦዲት መገኘቱንም ገልጸዋል።
በተከናወነው የኦዲት አፈጻጸም ክትትል በታዩት ግኝቶች ላይ አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ጠቅሰዋል።
በ16 መሥሪያ ቤቶች ላይ በተደረገ ክትትልም በኦዲት ሪፖርቱ በተሰጠው የማሻሻያ ሐሳብ መሠረት የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቁመዋል።
በ2019 በጀት ዓመትም ለብልሹ አሠራር ተጋላጭ በሆኑ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ውስጥ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የኦዲት አገልግሎት ይጠናከራል ብለዋል።
በክልሉ የበጀት፣ የንብረትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በእጥፍ እየጨመረ በመሆኑ የመሥሪያ ቤቱ ባለሙያዎችን አቅምና ብቃት ማሳደግ፣ የንብረት ክትትልና ቁጥጥርን ማጠናከር እንዲሁም የኦዲት ሽፋንን ማሳደግ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ጨፌ የመንግሥት በጀትና የሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴም የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የተለያዩ የኦዲት ዓይነቶችን ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጿል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ገመቹ አራርሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፤ የመንግሥት አሠራር ባልተከበረባቸው ቦታዎች ላይ በኦዲት ግኝቶች ላይ የተመሠረተ እርምጃ እንዲወሰድ ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026