🔇Unmute
ሰቆጣ፤ ሃምሌ 18/2018(ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 34 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአስተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ ለኢዜአ እንደገለፁት አካባቢው ዝናብ አጠር በመሆኑ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በስፋት በመገንባት ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከ539 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ 34 የመስኖ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል።
የተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶችም 820 ሄክታር መሬት በማልማት ከአራት ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ፕሮጀክቶቹ በብሄረሰብ አስተዳደሩ በበጋ ወቅት ጭምር በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
ስራ የጀመሩት ፕሮጀክቶች አርሶ አደሩ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ አትክልትና ፍራፍሬ ጨምሮ እንዲያመርትና የስርዓተ ምግብ ችግር እንዲያቃልል የሚያደርግ መሆናቸውንም ጨምረው ገልፀዋል።
የሰቆጣ ከተማ የ03 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ንጉሱ አመረ እንዳሉት፤ በአካባቢያቸው የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ከዝናብ ጥገኝነት በመውጣት በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ የማምረት አቅም እንድናገኝ የሚያደርግ ነው ።
የጓሮ አትክልትና ፍሬፍሬ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ምርቶችን በማሳደግ አኗኗራቸውን ለመቀየር የሚያስችላቸው መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።
በአስተዳደሩ በጋዝጊብላ ወረዳ 03 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አገኘሁ ጌታሁን፤በቀበሌያቸው የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት በክረምት ዝናብ ብቻ የተመሰረተውን የግብርና ስራ በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚነታችን እንድናሳድግ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
በብሄረሰብ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት በተገነቡ የመስኖ ተቋማት አራት ሺህ 885 ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026