የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት ውጤት ተመዝግቧል

Jul 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ታርጫ ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠ ትኩረት ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን በታርጫ ከተማ እያካሄደ ነዉ።


ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ክንውን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳመላከቱት፤ የክልሉ ዋነኛ የኢኮኖሚ አቅም ለሆነው የግብርና ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

በበጀት አመቱ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ሜካናይዜሽን እና የክላስተር እርሻን በማስፋት ዘርፉን ለማዘመን የተሰራው ስራም መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል።

በመኸርና በልግ ወቅት እንዲሁም፣ በበጋ መስኖ በዋና ዋና ሰብሎች ከ801 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን ከ23 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ በስራስር፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንሰት ከ80 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ጠቅሰዋል።

በቡና፣ በሻይና ቅመማ ቅመም ልማትም ምርትን ለማሳደግ የተሰራው ስራ ፍሬያማ እንደነበር ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በበጀት ዓመቱ ከ61 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰዋል።


ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ከሚያስችሉ ግብዓቶች መካከል አንዱ የሆነውን ምርጥ ዘር በራስ አቅም ለማባዛት በተሰጠው ትኩረትም ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።

በሌማት ትሩፋት ዘርፍ በዶሮ፣ በማር፣ በወተትና በዓሳ መንደሮችን ማደራጀትና የተደራጀቱን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ጥረት መደረጉንም አንስተዋል።

ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የመጠባበቂያ እህል እና መጠባባቂያ ፈንድ የማሰባሰብ ስራ በትኩረት መሰራቱንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የክልሉን የገቢ አቅም በማሳደግ የታቀዱ የልማት ግቦችን ለማሳካት በተደረገ ጥረት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

ከስራ እድል ፈጠራ አንፃርም በበጀት ዓመቱ ለ78 ሺህ በላይ ወጣቶችን በገጠርና በከተማ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተዉ፣ ለወጣቶቹ የመስሪያና መሸጫ ቦታዎችን የማመቻቸት እንዲሁም የብድር አቅርቦት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026