የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በክልሉ 51 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ ተችሏል

Jul 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ):-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 51 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የመስኖ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አየልኝ መሳፍንት ለኢዜአ እንዳሉት፤ በክልሉ ዘመናዊ የመስኖ አውታሮችን ግንባታ በማስፋት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እየተሰራ ይገኛል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም አርሶ አደሩን ከባህላዊ አሰራር በማላቀቅ በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ ማምረት የሚችልበትን እድል ከማስፋት አንፃር የተሻለ ስራ ማከናወን ተችሏል ነው ያሉት።

ለመስኖ ልማት የሚውሉ አካባቢዎችን በጥናት ከመለየት ባለፈ ወደ ግንባታ በማስገባት አርሶ አደሩ የዘመናዊ መስኖ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ መቻሉንም አብራርተዋል።

በተቀናጀ መንገድ በተደረገ ጥረትም 90 የመስኖ ፕሮጀክቶችን ወደ ግንባታ ማስገባት መቻሉን ጠቅሰው፤ ከእነዚህ ውስጥ 51 የሚሆኑትን በማጠናቀቅ ለልማት ስራ እንዲውሉ ለማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።

ግንባታቸው የተጠናቀቁ የመስኖ ፕሮጀክቶችም ከ3 ሺህ 400 ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ያስቻሉ ሲሆን ከ 7 ሺህ 500 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሆኑም ገልፀዋል።

በተጨማሪም ከ30 ሺህ ሄከታር በላይ መሬት ማልማት የሚችሉ 99 የመስኖ ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይንን በማጠናቀቅ ለግንባታ ስራ ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል።

የመስኖ አውታሮችን በማስፋት የአርሶ አደሩን ትርፍ አምራች በማድረግ የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ አቅሙን የማሳደግ ስራ ታሳቢ ተደርጎ እየተከናወነ ነው።

እንዲሁም እንደ ሀገር በምግብ እህል ራስን የመቻል ግብ እንዲሳካ በሚያግዝ አግባብ እየተከናወነ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ለመስኖ ተቋማት ግንባታና ተያያዥ ስራዎች ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ መደረጉንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አስታውቀዋል።

በአዲሱ በጀት ዓመትም ቀደም ሲል ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት ዕቅድ ተይዞ ወደ ስራ እየተገባ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ በመስኖ መልማት የሚችል ከ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት እንዳለም ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ተደርጓል

ድሬደዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን የድሬደዋ አስተዳ...

Jul 20, 2026

በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት እየጣለ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት መጣል መቻሉን የፌ...

Jul 7, 2026

በተያዘው ዓመት በኢንዱስትሪው የተኪ ምርቶች አቅርቦትን በማሳደግ 5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ):-በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተያዘው ዓመት የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግና የውጭ ምርቶችን በመተካት አምስት ቢሊዮን ዶላር ...

Jul 3, 2026

ቡናን በበጋ መስኖ በማልማት የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል

አዳማ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ቡናን ከመደበኛ ወቅት በተጨማሪ በበጋ መስኖ በማልማት የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት መደ...

Jun 17, 2026