🔇Unmute
ሮቤ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦የጨልጨል መስኖ ፕሮጀክትን በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት እየተሰራ መሆኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ እየተገነባ ያለውን የጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።
ፕሮጀክቱ በተቋራጭ የአቅም ውስንነትና በዲዛይን ለውጥ ምክንያት ተጓቶ የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍና አዲስ ተቋራጭ በመተካት የግንባታ ሥራው እንዲቀጥል ተደርጓል።

በሚኒስቴሩ የመስኖ ፕሮጀክቶች ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ሊካሳ እንዳሉት፤ የጨልጨል መስኖ ፕሮጀክትን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ቀጥተኛ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነው።
በ2012 ዓ.ም የግንባታ ሥራው የተጀመረው የጨልጨል መስኖ ፕሮጀክት በ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰዋል።
የመስኖ ፕሮጀክቱ በዲዛይን ችግርና በተቋራጭ የአቅም ውስንነት ምክንያት መጓተቱንም ነው የገለጹት።
የመስኖ ፕሮጀክቱ በተለይ በቅድመ-ዕቅዱ በአነስተኛ መስኖ ደረጃ ሊገነባ ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ የልማት አቅሙንና ደረጃውን ከፍ ለማድረግ በተደረገው የዲዛይን ማሻሻያ ምክንያት ግንባታው ለተወሰኑ ጊዜያት ቆሞ እንደነበር አንስተዋል።
እንዲሁም ከተቋራጭ የአቅም ውስንነት ጋር ተያይዞ ያገጠመውን ችግር ለመቅረፍ ፤የነበረውን ተቋራጭ ውል በማቋረጥ በዘርፉ ልምድና አቅም ያለው ተቋራጭ ስራውን እንዲቀጥል መደረጉን አመልክተዋል።
የጨልጨል መስኖ ፕሮጀክት በሁለት ሎት ተከፋፍሎ እየተገነባ ሲሆን፤ አንደኛው የግድቡ ግንባታ ሁለተኛው ደግሞ የመስኖ ካናል ዝርጋታ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅትም 4 ሺህ 145 ሄክታር ማልማት የሚችለው የካናል ሥራ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን የተጓተተውን የግድቡን ሥራ በማጠናቀቅ ወደ ሥራ ለማስገባት ትኩረት መደረጉን አክሏል።

የፕሮጀክቱን ግንባታ በአዲስ መልክ እያከናወነ የሚገኘው የአለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ፕሮጀክት ማኔጀር ኢንጂነር ባህሩ ፊኖ በበኩላቸው ፕሮጀክቱን በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ በሙሉ አቅም እየሰራን ነው ብለዋል።
የፕሮጀክቱ ማነቆ የነበረው የዲዛይን ችግርና የግድቡ መሰረት የሙሌት ማሽን እጥርት ተፈትቶ ቀሪ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
የፕሮጀክቱ አሁናዊ አፈጻጻም 50 በመቶ መጠናቀቁን የገለጹት ኢንጂነር ባህሩ ለግድቡ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ በመዘጋጀታቸው በ2019 የበጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የጨልጨል መስኖ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ባሌ ዞን ዝናብ አጠር በሆነው ቆላማ የራይቱ ወረዳ አካባቢ ነው እየተገነባ የሚገኘው።
የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ 4 ሺህ 145 ሔክታር መሬት በማልማት ከስምንት ሺህ በላይ አርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ድሬደዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን የድሬደዋ አስተዳ...
Jul 20, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት መጣል መቻሉን የፌ...
Jul 7, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ):-በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተያዘው ዓመት የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግና የውጭ ምርቶችን በመተካት አምስት ቢሊዮን ዶላር ...
Jul 3, 2026
አዳማ፤ ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ቡናን ከመደበኛ ወቅት በተጨማሪ በበጋ መስኖ በማልማት የአምራቹን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት መደ...
Jun 17, 2026